2015-06-03 17:19:00

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፤ ዓለማችን አለቤተሰብ አረሜናዊት ናት፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናንና ነጋድያን በቤተሰብ ዙርያ የጀመሩትን ትምህርት በመቀጠል ዛሬ ደግሞ በቤተሰብና ድህነት መካከል ያለውን ግኑኝነት አስመልክተው “ፖሎቲካና ምጣኔ ሃብት ከቤተሰብ የሚገኘውን መልካም ውጤት ለማየት የማይችሉበት ምክንያት በስስት ስለታውሩ ሲሆን ጠንቅቆ ለሚመለከት ግን ከቤተሰብ የሚገኘው መልካሙ ውጤት ከሁሉ አስቀድሞ በፍቅር የመተሳሰብና የመተሳሰር ማኅበረሰባዊ ዕሴት ሲሆን ይህ ደግሞ የሰው ልጆችን ልዩ በሆነ መንገድ የሚያስተሳስር ነው፣ ይህ መተሰሳሰርና መተሳሰብ ዓለማችንን አረሜናዊ ከመሆን ሲያድን በአንጻሩ ግን የዘመናችን የገዛ ራስ ምቾት የመፈለግ ዓላማዎች ቃልኪዳንና ቤተሰብን እንደ አደናቃፊ ነገር እንዲመለከት ያደርጋል፣ ሲሉ ካስተማሩ በኋላ መዘንጋት የሌለብን እውነት ቢኖር ቤተሰብ ብዙ ችግር እንዳለው እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣

“ቤተ ሰብን የሚፈታተኑ ብዙ ችግሮች አሉ፤ ከእነዚህ ችግሮች አንዱ ድህነት ነው፣ ከታላላቅ ከተማዎች በስተውጭ በድኃ አከባቢዎች የተመለከትን እንደሆነ ብዙ ቤተሰቦች በድህነት አለንጋ እየተገረፉ ነው፣ እንዲሁም በአንዳንድ የገጠር መንደሮች ስንት ድህነትና የተከፋ ኑሮ እንዳለ እናያለን፣ ነገሮችን እጅግ ለማባባስ ደግሞ በድህነት መማቀቅ አለበቃ ብሎዋቸው በአንዳንድ አከባቢዎች ጦርነት ይነሣል፣ ውግያ ሁሌ መጥፎ ነው፣ ጦርነት ሁሉንም ሲያጠቃ በይበልጥ የሚጐዳው ግን ቤተሰብን ነው፣ ይበታትናቸውል፣ እውነትም ጦርነት የድህነቶች ሁሉ እናት ናት፣ ጦርነት ቤተሰብን ያደሀያል፣ ብዙ የሰው ሕይወት የሚቆጭ ነፍሳትን የሚያስጨንቅና እጅግ የተቀደሱና ውድ የሆኑ የቤተሰብ ፍቅርንና መተሳሰርን ያጠፋል፣ በማለት ዋነኛው የድህነት መንሥኤ ጦርነት መሆኑን ገልጠው ዓለማችን ቤተሰብን ካልመረጠች ወደ አረሜንነት እንደምትለወጥ በማስገንዘብም ወይም ቤተሰብን ወይንም አረሜነትን ምረጡ ብለዋል፣

“ዓለማችንን በሚያማቅቁ ጦርነትና ድህነት አንጻር ደግሞ ብዙ ድኃ ቤተሰቦች በታላቅ ክብር ዕለታዊ ሕይወታቸውን ለመምራት በእግዚአብሔር ቡራኬ በመተማመን የሚታገሉ አሉ፣ ነገር ግን ይህ ሁኔታ የምናሳየውን ግድየለሽነት የሚያስተካክል አይደለም እንዲያው ባለው ብዙ ድህነት የሚሰማንን ኃፍረታችንን ማሳደግ አለበት እንጂ፣ ባለነው እንዲህ ባለ የድህነት ዘመን ገና ቤተሰብ ሲመሠረትና በታላቅ ትግል ወደፊት ሲራመድ ማየት ራሱ ታላቅ ተአምር ነው፣ ለዚሁ ምስጋና ይግባው ገና የሰው ልጅ መተሳስር እየቀጠለ ነው፣ ይህ ዓይነት ትግል ምናልባት የዘመናችን ሊቃውንትን ሊያስጨንቅ ይችላል ምክንያቱም እነኚህ ሊቃውንት ለግል ምቾትና መልካም ኑሮ ሲሉ የቤተሰብ መተሳሰርና ፍቅርስ ይሁን ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፈውን የዘር ሓረግ ለኑሮአችንና ለሕይወታችን በሁለተኛ ደረጃ የሚታዩ ናቸው ስለሚሉ፣ እኛ ግን በእነኚህ ቆራጦችና ለሰብአውነት ዋስትና በመሆን ብዙ በሚያስተምሩን ቤተሰቦች ፊት ተምበርክከን ልናመሰግናቸው ይገባል ለምን ብትሉ ዓለማችንን አረሜናዊት ከመሆን እያዳንዋት ናቸውና፣ ሲሉ አድናቆታቸውን ከገለቱ በኋላ ለገንዘብ ለዓመጽና ለጥቅም ስንል የቤተሰብን መተሳሰር መተሳሰብና ፍቅርን ያጠፋን እንደሆነ ምን ይዘን እንቀራለን? ሲሉ የምራቸውን ተናግረዋል፣ የማኅበራዊ ኑሮ አላፊዎች መለስ ብለው ሁሉን ነገር በአዲስ የግብረገብነትና የቤተሰብ መሠረት በመግንባት በቤተሰብና በድህነት መካከል ያለው እየላቀ የሚመጣውን ግኑኝነት ካልለወጡ ችግሩ ገና ነው፣ የዘመናችን ምጣኔ ሃብት ለግል ጥቅምና ምቾት ብቻ በማትኰር ቤተሰብን እየጨቆነ ነው፣ ፖሎቲካና ምጣኔ ሃብት ከቤተሰብ የሚገኘውን መልካም ውጤት ለማየት የማይችሉበት ምክንያት በስስት ስለታውሩ ሲሆን ጠንቅቆ ለሚመለከት ግን ከቤተሰብ የሚገኘው መልካሙ ውጤት ከሁሉ አስቀድሞ በፍቅር የመተሳሰብና የመተሳሰር ማኅበረሰባዊ ዕሴት ሲሆን ይህ ደግሞ የሰው ልጆችን ልዩ በሆነ መንገድ የሚያስተሳስር ነው፣ የሰው ልጅ ምሶሶውችም ናቸው፣ እነኚህን ካወገድን ሁሉ ይፈርሳል፣ ይህ የዳቦ ጥያቄ ብቻ አይደለም ሥራ ትምህርት ጤና ሁሉም ይነካል፣ ይህንን የምንገነዘበው በድህነት የሚማቀቁትን በመታዘብ ሲሆን ምንም አለማድረጋችን ግን ይህ መተሰሳሰርና መተሳሰብ ዓለማችንን አረሜናዊ ከመሆን ሲያድን በአንጻሩ ግን የዘመናችን የገዛ ራስ ምቾት የመፈለግ ዓላማዎች ቃልኪዳንና ቤተሰብን እንደ አደናቃፊ ነገር እንዲመለከት ያደርጋል፣ በአጠቃላይ የሁሉ መሠረት ቤተሰብ መሆኑን በማስታወስ ዙርያችንን ስንመለከት በድህነት እየተማቀቁ ያሉት ግን በትናንሽ ነገሮች ደስተኞች ሆነው የሚገኙትን እንመልከት ብለዋል፣

“በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በረሃብ እርዛትና ሕመም የሚሰቃዩትን ሕጻናት ስናይ እጅግ እናዝናለን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በእንዲህ ያለ ኢሰብአዊ ኑሮ የሚገኙ ሕጻናት አለምንም ነገር ለስሙ ትምህርት ቤት ተብለው በሚጠሩ ቦታዎች ሆነው እርሳሳቸውና ደብተሮቻቸውን በደስታ ሲያሳዩ አስተማሪውቻቸውን በታላቅ አክብሮትና ፍቅር ሲመለከቱ ማየት እውነትም የሰው ልጅ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ለማለት ያስችላል፣ ይህ ሁሉ የቤተሰብ መተሳሰርና መተሳሰብ ስላለ በፍቅር ስለሚሞቁ ነው፣ ይህ የጐደለ እንደሆነ ሕጻናቱ ምንኛ ያህል እንደሚሰቃዩ ማሰቡ አያዳግትም፣ እኛ ክርስትያኖች በድህነት የተቸገሩና በታላቅ ፈተና የሚገኙ ቤተሰቦችን ማየትና እጐናቸው በመሆን መርዳት አለብን፣ አስተውላችሁ አከባቢያችሁን ዳስሱ ስራ ያጣ አባት ሥራ የሌላት እናት ካሉ ቤተሰቡ እንደኤት እንደሚሰቃይ የቤተሰብ መተሳሰሩ እንደሚላላ እወቁና እንድትረድዋቸው ይሁን፣

“ማኅበራዊ ድህነት ቤተሰብን ያጠቃል አንዳንዴ ያወድመዋልም፣ ሥራ አጥነት ከሥራ መባረር ሌላ ሥራ ማግኘት የማይቻል ሲሆን በቤተሰብ ላይ ታላቅ ጫና ያወርዳል፣ ቤተሰቡ ይፈተናል፤ ድሆች በሚኖርዋቸው አከባቢዎች ሕይወት እጅግ ከባድ ነው የሥራ ጉዳይ የትራንስፖርት ጉዳይ ማኅበራዊ አገልግሎቶችና የጤና ጉዳዮች እጅግ አሳሳቢ ይሆናሉ፣ በእነዚህ ላይ ደግሞ የዘመናችን የህልም ኑሮ ዓይነት የመቃኘቱ ጉዳይ በክበድ ላይ ክበድ ይጨምራል፣ ስለዚህ ቤተሰብን እንንከባከብ የቤተሰብ መተሳሰርንና መተሳሰብን እንንከባከብ፣ ድህነት ቤተሰብን ይፈታናልና፣

“ቤተ ክርስትያን እናት ስለሆነች ይህንን የልጆችዋ ድራማን መርሳት የለባትም፣ እርሷም ከድሆች ድኃ መሆን አለባት፣ አንዲት ድህ የሆነች ቤተክርስትያን ልጆችዋን ቀለል ባለ መንገድ መረዳትና መርዳት ትችላለች፣ ማንኛውንም የመለያየት ግድግዳን ትደረምሳለች፣ ጸሎትና ተግባር ያስፈልጋሉ፣ የዚህ አስፈላጊነት በመረዳትም እግዚአብሔር ቤተሰቦቻችንን እንዲጠብቅ እንለምን፣

“የድሆች ፍርድ የእግዚአብሔር ፍርድ መሆኑ አንርሳ፣ የትናንሾችና የድሆች ፍርድ የእግዚአብሒርን ፍርድ ይቀድማል፣ ይህንን አንርሳ! ለቤተሰቦች የተቻለንን ያህል እናበርክት፣ ቃለ እግዚአብሔር የሚለውን እንደገና ላሳስባችሁ እወዳለሁ “ልጄ ሆይ ለድሃ ለሕይወቱ የሚያስፈልገውን አትንፈግለት፣ በችግር ላሉ ሰዎች ደግሞ ደንዛዛ አትሁን፣ የተራበውን ችላ አትበል በችግር ያለውን ዝም ብለህ አትመልከት ተቸግሮ የሚለምንህን ሳትሰጥ አትለፍ፣ እርዳታ ለሚጠይቅህ ስጥ አለበለዚያ እንዲረግመህ ዕድል ትሰጠዋለህ ይህ ደግሞ የጌታ ፍርድ ነው፣ ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣ 








All the contents on this site are copyrighted ©.