2015-05-29 17:08:00

ብፁዕ አቡነ ቲገ፦ ግኑኝነት አንዱ የሰብአዊ ድል


ግኑኝነት የግብረአዊ ሙያ ወይንም የዕደ ጥበብ ውጤት ከመሆኑ በቅድሚያ ሰብአዊ ድል ነው፣ ጳጳሳዊ የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ የቫቲካን የመገናኛ ብዙኃን የኅዳሴ ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት አባል ብፁዕ አቡነ ፓውል ቲገ በጀነቭ ዓለም አቀፍ የማስታወቂያ ኅብረተሰብ በሚል ርእስ ሥር በመካሄድ ላይ ባለው ዓውደ ጉባኤ ተገኝተው ባስደመጡት ንግግር ገልጠው፣ በሥነ አኃዝ በተራቀቀውና በመራቀቅ ወደ ፊት እያለ ስላለው የማኅበራዊ የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ማእከል በማድረግ፣ አዳዲስ የዕደ ጥበብ ውጤቶች የሚደነቁም የሰው ልጅ ጥበብና ግብረአዊ ሙያ የደረሰበት ደረጃ የሚመሰክር ነው። ቢሆንም ሰው በሱታፌ ጥበብ የተካነ በመሆኑ ብቃቱ ለግል ጥቅም ሰውንና ተፈጥሮን ለሚጎዳ ተግብር መገልገያ ለማድረግ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔ ፈጣሪ መሆን ሱታፌ አማካኝነት እንዲኖረው እግዚአብሔር የሰጠው ጸጋና ጥሪ በመሆኑ ለእድገትና ለተሻሻለ ኑሮ ለሁሉም ሰው ዘር ጥቅምና ተፈጥሮንም ለመንከባከብ የሚያገለግል መሣሪያ መሆን አለበት እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

በሥነ አኃዝ የተራቀቀው አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን መሣሪያ ተጠቃሚው የበለጸገው ዓለም ብቻ መሆን የለበትም። በዚህ በሥነ ምርምር ደረጃ የሚደረሰው ብልጽግና የሁሉም ለሁሉም መሆን አለበት። ያልበለጸገው ዓለም የዚህ እድገት ተጠቃሚ እንዲሆን መደገፍ አለበት፣ ካልሆነ ለብቻ የሚደረግ እድገት ላጭር ጊዜ ድል ሊመስል ይችል ይሆናል፣ ቆይቶ ግን የውድቀት ምልክት እንደሚሆን አይቀሬ ነው። በሁሉም መስክ የሚረጋገጠው እድገት ሰብአዊነት ማእከል ያደረገ መሆን አለበት። ካልሆነ የዕደ ጥበብ እድገት ብቻ ሆኖ ይቀራል። አለ ሰብአዊነት ሲሆን ጉዳት እንደሚሆን ገልጠው ቤተ ክርስቲያን በሕንጸት ጎዳና ሁሉም ሰው የዕደ ጥበብ እድገት ተጠቃሚ እንዲሆን ድጋፍ በማቅረብ በዚሁ የአገልግሎት ዘርፍ የዓለም አቀፍ መንግሥታት ጭምር በማነቃቃት የዕደ ጥበብ እድገት የሰላም የእውነተኛ ግኑኝነት የትብብርና የመደጋገፍ መሣሪያ መሆን ይገባዋል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።    








All the contents on this site are copyrighted ©.