2015-05-25 16:45:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የወጣቱ ሥራ የማግኘት መብትና ክብር ገንዘብ ጌታው በሚያደርግ ባህል አትሰዉ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ እ.ኤ.አ. ግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. የኢጣሊያ የክርስቲያን ሠራተኞች ማኅበር ዝክረ 70ኛው ዓመተ ምሥረታው ምክንያት በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው እጅግ ፈጣን በሆነ አካሄድ እየተስፋፋ ያለው የእኩልነት አልቦ ሂደት በምንም ተአምር ተቀባይነት የሌለው የሥራውና የሠረተኛው ዓለም የሚጎዳ ብቻ ሳይሆን በዚህ ዓለማዊነት ትሥሥር በተረጋገጠበት ዓለም ሁሉንም የሚነካ ነው። ስለዚህ ይኸንን እክል በተስተካከለ በመተሳሰብ ባህል አማካኝነት ምላሽ ሊሰጠው ይገባል የሚል ቅዉም ህሳብ ላይ ያነጣጠረ መሪ ቃለ መለገሳቸው የቫቲና ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ ሳባቲነሊ ገለጡ።

የሥራ ዕጦት የማያስተማምን የሥራ ኤኮኖሚ በሕገ ወጥ መንገድ ሠራተኛ መቅጠር ጥቁር ሥራ መስፋፋትና ይኸንን የማያስተማምን ሁኔታ የወንጀል ቡድኖች በቀላሉ ሌላውን ለመበዝበዝና ለራስ ጥቅም ለማዋል እንዲችሊ የሚያበረታታ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ሲያሳስቡ፦

ወጣቱ ሥራ የማግኘት መብት ገንዘብ ጌታው ለሚያደርግ ባህል አትሰዉ

ቅዱስ አባታችን ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ሂደት የሰው ልጅ ማእክል ከማድረግ ይልቅ ገንዘብ ጥጣት በማድረግ፣ ጌታው ገንዘብ ያደረገ በመሆኑ፣ በዚህ ትርፋትርፍ የሚያምን ባህል ሌላውን እንደ ጥራጊ እንደ ግኡዝ ነገር ተጠቅሞ መጣል ለሚለው ባህል የሚያጋልጥ፣ ሁሉንም እንደ ጥራጊ መጣል፣ መጀመሪያ የሚወለደው ሕጻን እንደ ንብረት በማየት በራስ ጥቅም አንጻር ያንን ተወላጁ ሕጻን በመመልከት ይወለድ ወይ ገና ሳይወለድ ይቀጭ ብሎ መፍረድ፣ በእድሜ የገፋው ከጥቅም አንጻር በማየት እንደ ጥገኛ ለኤኮኖሚ መቃወስ ምክንያት አድርጎ በመመልከት ካልሆነም ክብር ለሌለው የጡረታ አብል በማጋለጥ እንደ ጥራጊ በመልከት የገንዘብ ሃብት ማካበት የሚል ነው። ይባስ ደግሞ ወጣቱ ትውልድ በማያስተማምን ሁኔታ እንዲኖር ሥራ የማግኘት እድል እንዳይኖረው በሥራ አጥነት ችግር እንዲጠቃ በማድረግ ወጣቱ ትውሉድ ሳይቀር እንደ ጥራጊ መመለከት ለራስ ጥቅም መገልገያ የማድረጉ ምርጫ እየተስፋፋ ነው። ይኽ ሁሉ በዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ስልት ገንዘብ ተመላኪ መሆኑ ያረጋግጥልናል ብለዋል።

ሥራ ነጻ የፈጠራ ብቃት ያለው አሳታፊና መተሳሰብ የሚል መሆን አለበት

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተሰየሙበት ሰዓት ጀርመው ሥራ የሰው ልጅ ክብር ነው በማለት በመደጋገም የሚያሰሙት ቃል፣ ይኸው የኢጣሊያ ክርስቲያን ሠራተኞች ማኅብራት ተቀብለው በለገሱት መሪ ቃል በማስተጋባት፣ ወንጌል በኃሴት በተሰየመው በደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን፥ ሰው በሥራ አማካኝነት የገዛ እራሱ ሕይወት ክብር ይኖራል ያጎለብታል ያሉትን ሃሳብ ጠቅሰው፣ ነጻ ሥራ ሲባል፣ ሰው የእግዚአብሔር ተግባር ተሳታፊ የመሆን ጥሪው በመኖር፣ ዓለም ተገቢ ፍጻሜ እንዲያገኝና እርሱም የእግዚአብሔር ሥራ የሚል ፍጻሜ መሆኑ ገልጠው፣ እግዚአብሔር በፈጸመው ተግባር በፍጥረትና በሰው ልጅ ታሪክ ህላዌውንና አርአያነቱን ስጋ እንዲለብስ በማድረግ በእያንዳንዱ ሰው አማካኝነት ቀጣይነቱንም ያረጋግጣል፣ ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ሥራ በተለያየ መልኩ የብዝበዛ መሣሪያ እየሆነ እወተኛው ትርጉም እንዲስት እየተደረገ ነው። የአዳዲስ ባርነት ምንጭ ድኾችን የሚጨቁንና የሚበዘበዝ ሕጻናት ሴቶች ክብር ለሚሰርዝ ተግባር የሚያጋልጥ ወይንም ሰብአዊ መብታቸውን ግምት ሳይሰጥ ለሥራ ዓለም የመዳረጉ ጉዳይ የመሳሰሉትን ጠቅሰው ይኽ ሁሉ ሥራ የውህደትና የውበት መሣሪያ የሚለው ትርጉሙ የሚጻረር ነው። ሥራ የተስፋና የአዲስ ሕይወት መሣሪያ እንጂ የአድልዎና የመነጠያ መሣሪያ መሆን የለበትም እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሳባቲነሊ ገለጡ።

ወጣት ትውልድ ብዙ የሚሰጥ አበርካች ነውናን ክንፉን እትንጨቁ

የሥራ፣ የፈጠራ ብቃት፣ በሥራ አማካኝነት እያንዳንዱ ዜጋ እግዚአብሔር በልቡ ያኖረለትን መልካምነት እግብር ላይ ያውላል። በዚህ ዓይነቱ ሂደት የሚመራ የሥራ ዓለም ወይንም ሰው ይኸንን መለያውን በተለያየ ሥራ ሲገልጠው፣ ለማኅበርሰብና ለሌሎች ሰዎች ሙሉ የኤኮኖሚና ማኅበራዊ እድገት ማረጋገጫ ይሆናል።

የወጣቱን ሰባ መንጨቅ አይገባም፣ ወጣቱ ትውልድ ባለው ብቃት ብልህነት ተክኖ ብዙ የሚሰጠው አለው። ወጣቱ ወደ ሥራ ዓለም በሙሉ መብት እንዳይገባ ከሚያግደው ተግባር ሁሉ ነጻ ማውጣት የሁሉም ግዴታ ነው።

ተሳታፊነት ያለው ሥራ ሰው በተጨባጩ ዓለም ቅርጽ እንዲያሳድር በሥራው ዓለም ተምሳዩን የሚያስተውል ይኽ ደግሞ ተገናኝ የመሆን መለያው እግብር የሚያውልበት፣ የሥራ ፍጻሜ ሌላውን ማክበር መመልከት ስለ ሌላው ማሰብና ከሌሎች ጋር የመተባበር ኃላፊነት መኖር የሚል ነው። ሥራ የእግዚአብሔር ተግበር ቀጣይ የሚል ሥራ ለሁሉም ሰው ልጅ ምክንያቱ ሁሉም የሥራ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስገነዝበው የሥራ ቀዳሜ ትርጉሙ የሚያኮላሽ  ያ ሌላውን እንደ መሣሪያ መጠቀም የሚለው ተስገብጋቢው ኤኮኖሚ መቃወም ማለት ነው።

በሥራ አጥነት ከሥራ ዓለም ለሚባረረው ቅርብ መሆን

በየቀኑ ወደ ቤቱ የዕለት እንጀራውን ይዞ መግባት የሚፈልግ የቤተሰብ አባት የቤተሰብ እናት ከሥራ የሚባረር በሥራ ዕጦት ከተጠቃ ዜጋ ጋር እንገናኛለን፣ ለእነዚህ ዜጎች ላለባቸው ችግር ተገቢ መልስ መሰጠት ያስፈልጋል፣ ሥራ የትብብር መንፈስ የሚል፣ ስለ ሌላው ማሰብ የሚል ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን፣ በቅድሚያ በችግር ለተጠቃው ቅርብ መሆን የሠራተኛ ማኅበራት አገልግሎትም እርሱ ነው። ቅርበት መግለጥ ሌላው ሥራ ለማግኘት የሚያበቃ መሣሪያ ማቅረብ። ነጻነት የፈጠራ ችሎት ተሳትፎና መተባበር የክርስቲያ ሠራተኞች ማኅበር መለያ ነው። ዛሬ ስለ ሁሉ ሰብአዊ ክብር ገዛ እራሱን ሳይቆጥብ የሚያገለግል ማኅበር ማለት ነው። ይኽ ክርስቲያናዊ አገልግሎቱ አደራ በጽናት መኖር አለብን እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሳባቲነሊ ገለጡ።

ስለ ድኾች ስለ ሚነጠሉት እንደ ጥራጊ ስለ ሚታሰቡት ስለ ሚበዘበዙት ስለ ሚጨቆኑትን ሁሉ እናስብ። ማሰብ ብቻ ሳይሆን ከዚህ ወጥመድ ለማላቀቅ የሚያበቃ ኅብረተሰብ ለመለወጥ ብቃት ያለው አገልግሎት ማቅረብ የሁሉም ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ብለው በዚህ በአሁኑ ወቅት በኢጣሊያ ያለው የሥራ ሁኔታ በመዳሰስ የክርስቲያን ሠራተኞች ማኅበር በክርስቲያናዊ ሕይወት አስተንፍሶ ለሠራተኛው ለዴሞክራሲው ለቤተ ክርስቲያን ያላቸው ታማኝነት ለድኾች ታማኝ አገልጋይ በመሆን እንዲመሰክሩት አደራ በማለት የለገሱት ቃል ማጠቃለላቸው ልእክት ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ ሳባቲነሊ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.