2015-05-20 16:38:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ምግባረ ብልሽትና ሙስና ለማውገዝ አትፍሩ


እ.ኤ.አ. ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም. የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ወንጌላዊ ኃሴት የተሰየመው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሐዋርያዊ ምዕዳን ማእከል በማድረግ  68ኛው ጠቅላይ ጉባኤውን በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በአዲሱ የሲኖዶስ የጉባኤ አዳራሽ ቅዱስነታቸው ባስደመጡት የመክፈቻ ንግግር በይፋ መጀመሩ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ይፋ በሚያደርጉት ሐዋርያዊ መልእክት ተጨባጭ ያልሆነ ረቂቅ ሃሳብ የሚያቀርቡ እንዳይሆኑ፣ በኢጣሊያ ሰበካዎች ዓለማዊ ምእመን አንድ አቡን በሚያስፈልገው ጉዳይ የሚመራ ለአቡን ፍላጎት የሚያገለግል የማያደርግ ኃላፊነት የተካነው ሚና ብፁዓን ጳጳሳቱ እንዲያሳይሉ አደራ እንዳሉ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ገለጡ።

ለድኻው የኅብረተሰብ ክፍል ጠበቃ መሆን

ቅዱስ አባታችን በዚህ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ይፋዊ ጠቅላይ ጉባኤ ለማስጀመር ባሰሙት ንግግር፣ አንድ አቡን ከክርስቶስ የልብ ትርታ ጋር የተወሃደ የክርስቶስ ስሜትና ፍላጎት እርሱም ስለ ሌላው በተለይ ደግሞ ስለ ተናቀው ስለ ድኻው የሚያስብ ኢየሱስ ክርስቶስ ያሳየው የትሕትና ጠባይ በሕይወቱ በተጨባጭ የሚኖር፣ የክርስቶስ ጥበብ የተካነ መኃሪ መሆን አለበት፣ ባጭሩ የቤተ ክርስቲያናዊ አስተዋይነት የሚኖር እንዲሆን ይጠበቅበታል። እንደ ደግና የዋህ እረኛ ሕዝበ እግዚአብሔርን ከዚያ መለያውና ሰብአዊ ክብሩን ከሚነጥቁት ከተለያዩ የርእዮተ ዓለም ቅኝ ግዛት ከስቃይና መከራ ለመከላከል ወደ ሕዝበ እግዚአብሔር የሚወጣ መሆን አለበት።

የቤተ ክርስቲያናዊ አስተዋይነት በማሕበራዊና በግላዊ ሕይወት የሚዛመተው ቤተሰብን ቅን ሠራተኛው የኅብረተሰብ ክፍል ጡረተኛው ማኅበረ ክርስቲያንን ወጣት ትውልድ እንደ ጥራጊ የሚመለከት ለተጠቅሞ መጣል አደጋ የሚያጋልጥ ወጣቱን ለራስ ጥቅም ማዋል የሚለው ማንኛውንም ዓይነት ተስፋ ነጣቂ ባህል ድኻውንና ደካማው የኅብረተሰብ ክፍል የሚያገል ይኸ ጸረ ሰብአዊ ተግባር እንዲስፋፋ የሚያደረገው ምግብረ ብልሽትና ሙስና መሸማቀቅና መፍራት ብቃታ አልቦነት መቃወም የሚል ነውና የቤተ ክርስቲያን አስተዋይነት ይኑራችሁ ብለዋል።

ተጨባጭ ያልሆነውን እምቢ ማለት

ቅዱስ አባታችን ባስደመጡት ቃል ብፁዓን ጳጳሳት ተጨባጭ ካልሆነው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መቆጠብ ይገባቸዋል፣ ተጨባጭ ያልሆነ ሥነ ሃሳባዊ የቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ ትምርህት የጎላበትና ይኸንን የሚተነትን ለሕዝበ እግዚአብሔር ለተራው ሕዝብ ሳይሆን የላቁ ምሁራን ሊቃውንት በመሳብ የውይይትና የሥነ ሃሳብ ርእስ ብቻ ሆኖ የሚቀረው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ከመወጠን እደራ እንቆጠበ፣ ወደ ተጨባጭነት ሊለወጥ የሚችል ሁሉም ሊረዳው የሚችል መሆን አለበት እንዳሉ ደ ካሮሊስ ገለጡ።

በሌላው የማይነዱ ዓለማዊ ምእመን የሚያሳትፍ

ቤተ ክርስቲያናዊ አስተዋይነት በቤተ ክርስቲያን አጅግ አስፈላጊና መሠረታዊ ለሆነው በማንም በቆሞስ በብፁዓን ጳጳሳት በኤኮኖሚው በፖለቲካው ዓለም በመንግሥት በሌላው መዋቅሮችና ባለ ሥልጣናት የማይነዱ የዓለማዊ ምእመን ሚና ግምት የሚሰጥ በቤተ ክርስቲያን ባላቸው ብቃትና ጥሪ ማሳተፍ የሚል ነው።

አድነትና መግባባት

ቅዱስ አባታችን የሚያምኑበት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በመደጋገም ያሳሰበው የብፁዓን ጳጳስሳት ጉባእያዊነት የሚለው ርእስ፣ የቤተ ክርስቲያናዊ አስተዋይነት ክፍል መሆኑ ገልጠው፣ ጉባእያዊነት ማለት በብፁዓን ጳጳሳት ውህደትና ህብረት በሰበካዎች መካከል ውህደትና ኅብረት የጥሪና በቁሳዊ ነገር ሁሉ ሃብታም የሆኑት ሰበካዎች ከድኻው ሰበካ ጋር ውህደትና አድነት የከተሞቻችን ማእከላዊ ክፍል ከጥጋ ጥጉ የከተሞቻችን ክፍል ውህደት የሚል ነው። ይሕ ውህደትና ኅበረት ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር ጭምር የሚኖር መሆን አለበት። እንዲህ መሆን እየተገባው ነገር ግን በተለያዩ ሰበካዎች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለመወጠን በሚደረገው ሐዋርያዊ ተልእኮ ጉባእያዊነት ተጓድሎ ይታያል፣ የሰበካው ሁኔታ ሐዋርያዊ፣ የኤኮኖሚው ጉዳይ በጠቅላላ ለመወጠንና ሂደቱንም ለመገምገም በሚደረገው አገልግሎት ጉባእያዊ ለበስ አሠራር ሲጓደል ይታያል፣ ይኽ ደግሞ ሰበካዎች ቁምስናዎች ማኅበረ ክርስቲያን ለመከፋፈል አደጋ ያጋልጣል፣ የውህደትና የአንድነት ትእምር በሆነው በመንፈስ ቅዱስፍ እስትንፋስ ተመርቶ ከማገልገል ይልቅ አለ ጉባእያዊነት አሰራር በአንዳንዱ አስተሳሰብና ፍላጎት የተመራ የሚለያይና የሚከፋፍል  ተግባር ይሆናል፣ ይኽ ዓይነቱ አገልግሎት አገልግሎት ሳይሆን መገልገል ማለት ነው እንዳሉ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።

የገዳማዊ ሕይወት እርጅና እንዲቀረፍ ማገልገል

ቅዱስ አባታችን ባስደመጡት መልእክት ፍጻሜ እያረጁ በመሄድ ላይ የሚገኙትን የጥሪ እጥረት የሚታይባቸው ገዳማት መንፈሳዊ ማኅበራትና የልኡካነ ወንጌል ማኅበራት ጉዳይ በአንድ አገር የሚኖር ብሔራዊ ጉዳይ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ ችግር ነው። ስለዚህ ጊዜው እያለ አሁኑኑ ለምን እነዚህ ያረጁት ገዳማት ወይንም መንፈሳዊ ማኅበራት እንዲወሃዱ አይደረግም? ማኅበረ ክርስቲያን ካህናት ብፁዓን ጳጳሳት የዚያ ሞትን አሸንፎ የተነሳው ክርስቶስ ደስተኛ በቃልና በሕይወት መስካሪያን ለመሆን የተጠሩ ናቸው፣ ስለዚህ በጊዜ አመጣሽ የሚመሩ ሳይሆን ልሙድና ቅቡል የሆነውን አታላይ አመለካከትና አስተሳሰብ ጋር ተመሳስሎ መኖር ሳይሆን ይኸንን የሚቃወም በኃሴት የኃሴት ወንጌል መስካሪያን መሆን ይገባል እንዳሉ ደ ካሮሊስ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.