2015-05-18 15:57:00

በኢጣሊያ ቨነዚያ ከተማ የብፅዕና አዋጅ


የቨነዚያ ተወላጅ የቅዱስ ዮሴፍ ደናግል ማኅበር መሥራች አባ ልዊጂ ካቡርሎቶ እ.ኤ.አ. ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. በቨነዚያ ከተማ ቅዱስ ማርቆስ አደባባይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በወከሉት የቅድስና ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ብፅዕና እንዳወጀችላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ባርቢ አስታወቁ።

ብፁዕ ካቡርሎቶ እ.ኤ.አ. በ 1817 ዓ.ም. በኢጣሊያ ቨነዚያ ከተማ የተወለዱ የቨነዚያ ሰበካ ካህን ቤተ ክርስቲያን ብፁዕና ያወጀችላቸው ሁለተኛ የከተማይቱ ካህን መሆናቸው ያስታወሱት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ባርቢ አክለው፣ መጻኢ የጨለመባቸው የጎዳና ተዳዳሪ ወጣት ዜጎች ከህግና ሥርዓት ውጭ የሚኖሩትን ሁሉ በመንከባከብ ሰብአዊና ክርስቲያናዊ ሕንጸት በማቅረብ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ እግዚአብሔር ያገለገሉ፣ ሕንጸት ማፍቅር ማለት መሆኑ ሕንጸት ማቅረብ የአፍቃሪው የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር መኖር ማለት መሆኑ በቃልና በሕይወት የመሰከሩ። ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወታቸው ማከል በማድረግ እረኛ ካህን በመሆን ጥሪያቸውን በሙላት በጌታ ጸጋ የኖሩ መሆናቸው ብፁዕ ካርዲናል አማቶ ባሰሙት ስብከት እንዳሰመሩበት አስታውሰው፣ ወንጌል በታማኝነት በመኖር  ወጣቶችን በጌታ ፈቃድ ብርሃን እንዲመሩ በመደገፍ ማፍቀር እንጂ መፍረድ የእኛ አይደለም እያሉ ወጣት ትውልድ ከተጋለጠበት አደጋ እንዲላቀቅ የተጠመዱ የጌታ ፍቅር መስካሪ በማለት እንደገለጡዋቸው አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.