2015-05-18 15:44:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ ውፉያን ሃሴት የተካኑ የእግዚአብሔር ጸጋ ለዓለም


ዘንድሮ እ.ኤ.አ. 2015 ዓ.ም. በመከበር ላይ ያለው የውፉያን ዓመት ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በሮማ ሰበካ ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ቫሊኒ የተሸኑት በሮማ ሰበካው የሚገኙት የውፉያን ማኅበር አባላት ገዳማውያን ካህናትና ደናግል ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ገለጡ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የውፉያን ማኅበር አባላት የመሩት ለሮማ ሰበካ ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ቫሊኒ ውፉያኑን በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ፊት ለማቅረብ ካሰሙት ንግግር በመቀጠል፣ የመናንያን ሕይወት የመደበቂያ ሥፍራ ሳይሆን ለዓለም ክፍት የሆነ የተጋድሎና የትግል ቦታ ነው። እያንዳንዷ ገዳማዊት ድንግል የቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ምስል ነች። ብፁዓን አቡናትና ገዳማውያን ቤተ ክርስቲያን ጥዑም ውሁድ ባህርይ ትላበስ ዘንድ በሰበካቸው በመተባበር የሚኖሩ መሆናቸው የሚያበክር ቅዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ መሪ ቃል መለገሳቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አክለው፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በተካሄደው ግኑኝነት ከተሳተፉት ከ25 ሺሕ በላይ ከሚገመቱት ገዳማውያን ካህናትና ደግናል ውስጥ አንዳንዶቹ ላቀረቡላቸው ማኅበራዊና ሐዋርያዊ ሕይወት ላይ ያተኮረ ጥያቄ አንድ በአንድ መልስ መስጠታቸው አስታውቀዋል።

መናንያንና ውፉያን በእግዚአብሔር ውስጥ የሚደበቁ ከዓለም የማይደበቁ ናቸው በማለት የሰጡት መልስ የውፉይ ሕይወት ቲዮሎጊያ በጥልቀት የሚብራራ ሲሆን፣ ገዳማዊ ሕይወት ውፉይ  የተሰዋ ማለት እንጂ የተነጠለ ማለት አይደለም፣ በርግጥ ከገዳም ውጭ ያለው ሁኔታ የሚገልጥ ዜና ወደ ገዳሙ መድረስ አለበት፣ ሆኖም ተገቢ ዜና እንጂ አሉባልታና ሓሜት ሹኩቻ ነክ ዜና ይግባ ማለተ አይደለም። ከዓለም ጋር የሚያገናኝ መስመር ሊኖርው ያስፈልጋል፣ ብህትውና ዓለም ለሚያሰፈልገው ነገር ሁሉ ተግቶ እውነተኛው የሕዝብ ፍላጎት ጸሎት በማድረግ ለጌታ የሚያቀርብ ጸላይ ሕይወት መኖር ማለት ነው። የሕዝብ ስቃይ የሚስተነተንበት ስለ ሕዝብ የሚጸለይበት በመሆኑም የዓለም ተጨባጩ ሁነት ማወቅ ያስፈልጋል። በዓለም ነገር ግን የዓለም ሳይኮን የሚኖር ጸላይ ሕይወት ማለት ነው እንዳሉ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።

ገዳም የመደበቂያ ስፍራ አይደለም

በእግዚአብሔር ውስጥ በመደበቅ የሚለው የምንኩስናው ሕይወት ከዓለም መደበቅ ማለት አይደለም፣ የተደበቀ ሕይወት የሚኖርበት ጥሪ ማለት ሳይሆን የትግልና የተጋድሎ ጥሪ ነው። በመሆኑም በዓለም ከገዳም ውጭ ያለው ሁኔታ ሁሉ የገዛ እራስ በማድረግ ወደ ጌታ ልብ የሚንኳኳበት ሕይወት የሚኖርበት ጥሪ ነው። የብህትውና ሕይወት መኖር ማለት በተለያየ ችግር የገዳሙን በር ለሚያንኳኩ ክፍት ማድረግ ማለት ነው። በፈገግታ ኃሴት በተሞላው መንፈስ ለተጠማው ለተራበው የሚያስፈልገው ሁሉ መለገስ፣ መልካም እናደርግ ዘንድ ጌታ አዞናል። በመሆኑም ከግብረ ሰናይ የሚነጥል ጥሪ አይደለም ብለዋል።

አንዲት ድንግል እናት ነች

ገዳማዊ ሕይወት የምትኖር ድንግል እናትነት የምትኖር ነች፣ ገዳማዊ ሕይወት እናትነት ወይንም አባትነት መካድ ማለት አይደለም፣ አንዲት ድንግል ለክርስቶስ ያላት ፍቅር ልክ በምሥጢረ ተክሊል የሚኖር ፍቅር መግለጫ ነው። ማለትም ታማኝ ጽኑና በፈረቃ የማይኖር ዘላቂነት ያለው የልብ ታማኝነት የልብ አንድነት የተካነ ፍቅር የሚኖርበት ጥሪ ነው። ደናግል የቤተ ክርስቲያን ምስልና የቅድስት ድንግል ማርያም ምስል ናቸው። ቤተ ክርስቲያን በተባዕት ሳይሆን በአንስት ጾት የምትገለጥ መሆንዋ መዘንጋት የለብንም፣ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ ነች፣ የቤተ ክርስቲያን ፍቅር እናታዊ ፍቅር ነው። ይኽ ደግሞ የአንዲት ድንግል ፍቅር መግለጫ ነው። ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን የዋህነት የቤተ ክርስቲያን ታማኝነት የሚገለጥበት ጥሪ ነው። ቤተ ክርስቲያን እናት ስለ ሆነች የአንዲት ድንግል ፍቅር እናታዊ ነው። ምክንያቱም የቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅር ምስል ነውና።

ተጨባጭ ፍቅር፣ መልካምና እውነት

ፍቅር ርህራሄ ቢሆንም ተጨባጭ ነው። ተጨባጭነቱም የጌታ የተራራው ስብከት የሚገልጥ ነው። የቅዱስ ማቴዎስ ምዕ. 25 ጌታ ስለ ዓለም ፍጻሜ ፍርድ የሚናገረው ሁሉ የሕይወት መርሃ ግብር አድርጎ የሚኖር ፍቅር ማለት ነው። የጌታ ፍቅር፣ ጌታ የሚኖረው ፍቅር ለቤተ ክርስቲያን ለሰው ልጅ ሁሉ ተጨባጭ ፍቅር እንጂ ኅልዮ አይደለም። ፍቅር ተጨባጭና መልካምነት ነው። ስለዚህ ከዚህ በመንደርደር እውነት መናገር፣ እውነት በፍቅር መናገር፣ ፍቅር ጸላይ እንጂ አስመሳይነት የሚል አይደለም፣ ምክንያቱም እውነት ነውና።

ገዳማዊ ሕይወት ቅናት ምቀኝነት የሚኖርበት ሥፍራ ሊሆን ይችላል፣ የማኅበሩ ዓለቃ የሚታማበት፣ ስለ ሌላው የማኅበር አባል ሐሜት አቃቂር የሚነዛበት፣ እኔ ፊተኛ መሆን አለብኝ የሚባልበት ሥፍራ ሊሆን ይችላል፣ እውነተኛው መለያው ክርስቶሳዊ ሕይወት ነው። የገዳማውያን ማኅበራት በሰበካ የሚኖራቸው ሚና፣ ከሰበካ ጳጳስ ጋር የሚኖራቸው ግኑኝነት በጠቅላላ የጋራ ግኑኝነት የተሰየመው ጥንታዊው ሰነድ እ.ኤ.አ. በ 1994 ዓ.ም. የተካሄደው ሲኖዶስ ይታደስ ዘንድ ሃሳብ ያቀረበበት ሰነድ እግብር ላይ ማዋል እንዴት ያስፈልጋል።

የሁሉም መንፈሳውያን መርሆዎች አንድነት፣ ከካህናት ጋር አንድነት ከጳጳሳት ጋር አንድነት መኖር ያስፈልጋል፣ የእኔ ማህበር የእኔ ሰበካብ ማለቱ ሰብአዊ ነው። ሰዎች ነን፣ አንድ ጳጳስ ልክ እንደ አንድ ባላባት ገዳማውያን እንደ የችግር ማፈኛ ሊጠቀምባቸው አይገባም፣ ተፈላጊው ውህደት ነው።

ገዳማዊ ሕይወት የበዓል እንጂ የጫጫታ ሥፍራ አይደለም

በኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ 26 ያለው ታሪክ ማስታወስ ያስፈልጋል፣ የበዓል መንፈስ ጥልቅ ትርጉሙ በዚህ ምዕራፍ ተገልጧል፣ ስለዚህ በቅድሚያ ለእግዚአብሔር ከዛም ከሁሉም ጋር መቋደስ፣ በዓል አንዱ የሕይወት ቲዮሎጊያ ነው። አለ የሕይወት ቲዮሎጊያ የሚኖር ገዳማዊ ሕይወት የለም፣ በዓል ሲባል ጋጋታ ጫጫታና ዳንኬራ ማለት ሳይሆን፣ በኦሪት ዘዳምግ ምዕ. 26 ያለውን እናንብብ፣ በዚህ ምዕራፍ መጨረሻ ጥልቅ ጸሎት እናገኛለን፣ በዓል ጌታ ስላ ደረገልን ሁሉ የማስታወስ ደስታ፣ ሁሉ የሚሰጥ፣ ያ ለእርሱ መሥዋዕት አድርጌ የማቀርብለት ፍሬም የእርሱ ስጦታ ነው የሚል እውነት የሚመሰከርበት ሁነት ነው። የገዳማዊ ሕይወት በዓል ይኸንን ይመስላል፣ የሕይወት ቲዮሎጊያ።

የተአዝዞ ሚሥጢር

ተአዝዞ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ሚሥጢረ ሕይወት ማእከል ነው። የክርስቶስ ሚሥጢር የተአዝዞ ሚሥጢር ነው። መካን ተአዝዞ ሳይሆን ፍርያማ ተአዝዞ ነው። በውፉይ ሕይወት የሚኖር ተአዝዞ ሚሥጢር ነው። ተአዝዞ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መንገድ ነው። ከመጸነስ እስከ መስቀል የተኖረ ተአዝዞ ነው። የተአዝዞ ምሥጢር ለመረዳት የሚቻለው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተአዝዞ ነው።

መንፈሳዊ አባት ለዓለማውያን ምእመናን ክፍት የሆነ አገልግሎት ነው። የንሥሃ ምሥጢር የሚያካትት አገልግሎት የሚመለከት እንዳልሆነ በግልጽ በማብራራት፣ መንፈሳዊ ድጋፍ በካህን በዓለማዊ ምእመን የሚሰጥ አገልግሎት ሊሆን ይችላል።

ሴቶችና ቤተ ክርስቲያን

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የውፉያን ሕይወት  80 በመቶ በሴቶች የሚሸፈን መሆኑ በማስታወስ፣ የሴቶች ተሳትፎ በቤተ ክርስቲያን ከተባዕት ጾታ ጋር ውደራ የሚል ምርጫ ማለት እንዳልሆነ በማብራራት ያስደመጡት መሪ ቃል ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠና ደ ካሮሊስ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.