2015-05-18 15:48:00

ለግብረ ሠናይ የቤተ ክርስቲያን የበላይ መዋቅሮች ለሕዝብ እንጂ ለመገልገል አይደለም


የተለያዩ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የልማትና የማኅበራዊ አገልግሎት ማኅበራት የሚያቅፈው እ.ኤ.አ. በ 1950 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ የተመሠረተ ካሪታስ ኢንተርናዚናሊስ ማኅበር እ.ኤ.አ. ከግንቦት 12 ቀን እስከ ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. አንድ ሰብአዊ ቤተሰብ ተፈጥሮን መንከባከብ በሚል ርእስ ሥር 20ኛው ጠቅላይ ጉባኤ ማካሄዱ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ጉባኤው የካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ሊቀ መንበር በመሆን እንዲያገለግሉ በፊሊፒንስ የማኒላ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካሪዲንል ልዊስ አንቶኒዮ ታግለ የመረጠ መሆኑ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አክለው የእምነት ሰማዕት የእግዚአብሔር አገልጋይ ካርዲናል ኦስካር ሮመሮ አንዱ የዚህ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ማኅበር ተባባሪ ጠባቂ ቅዱስ በማለት እንደሰየመም አስታውቀዋል።

ከተካሄደው ጉባኤ ፍጻሜ በኋላ ይኸንን  የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ሁለቴ ሊቀ መንበር በመሆን ያገለገሉት በሆንዱራስ የተጉቺጋልፓ ሊቀ ጳጳሳት የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቤተ ክርስቲያን የበላይ ሐዋርያዊ መስተዳዳር መዋቅር ኅዳሴ ጉዳይ የሚከታተል ያቋቋሙት የብፁዓን ካርዲናሎች ምክር ቤት ሊቀ መንበር እንዲሆኑ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የተሾሙት ብፁዕ ካርዲናል ኦስካር ሮድሪገዝ ማራዲያጋ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ይኽ ማኅበር አለ ምንም ልዩነት ሰብአዊነት ማእከል በማድረግ በሁሉም ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ ችግር በሚታይበት ክልል በፍቅር ሥራ ተሰማርቶ የሚያገለግል ሰብአዊና መፍነሳዊ አገልግሎት የሚያቀርብ ነው። ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን አማካኝነት የሚገለጥ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግብረ ሠናይ ነው።

ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ደጋግመው ቤተ ክርስቲያን ወደ የከተሞቻችንና ወደ የኅልውና ጥጋ ጥግ ወደ ተነተጠለው ወደ ተናቀው ክልል ታቀና ዘንድ የሚሰጡት ምዕዳን የሚኖርበት የቤተ ክርስቲያን የግብረ ሠናይ መግለጫ ማኅበር መሆኑ ገልጠው፣ ግብረ ሠናይ አለ ምንም ገደብ ለሁሉም የሚል ነው ብለው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.