2015-05-15 16:46:00

ነፓል፦ በርእደ መሬት አደጋ የተጠቃው የኔፓል ሕዝብ እንዳይዘነጋ


እዚህ ሮማ እ.ኤ.አ. እስከ ግንቦት 17 ቀን የሚዘልቀው ግንቦት12 ቀን 2015 በተጀመረው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የልማትና የማኅበራዊ አገልግሎት ማኅበር 20ኛውን ጠቅላይ ጉኤው ለስምንት ሺሕ ዜጎች የሞት አደጋ ምክንያት የሆነው እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. በመቀጠልም ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በተከሰተው ተመሳሳይ የርእደ መሬት አደጋ ምክንያት ቤቱንና ንብረቱን ያጣው የነፓል ሕዝብ እንዳይዘነጋ ጥሪ ማቅረቡ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይላኒ ገለጡ።

የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እሁድ እ.ኤ.አ. ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. በመላ ኢጣሊያ ሰበካዎች ቁምስናዎችና አቢያተ ጸሎት በሚያርገው መሥዋዕተ ቅዳሴ የሚሰበሰበው ምጽዋት በርእደ መሬት አደጋ ለተጎዳው የነፓል ሕዝብ መርጃ የሚልው እንዲሆን ውሳኔ ማስተላለፉ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አስታወቁ።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም በዚህ በካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ይፋዊ ጠቅላይ ጉባኤ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት በነፓል በካሪታስ ለሚጠራው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበር ቅርንጫፍ አስተዳዳሪ ፒዩስ ፐሩማና ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በርእደ መሬት የተጎዳው ቤቱንና ንብረቱን ላጣው አለ መጠለያ ለቀረው የነፓል ሕዝብ ሙሉ ድጋፍ ማቅረብ ያስፈልጋል፣ መጠለያ ድንኳን የሕክምና የምግብ ባጠቃላይ መሠረታዊ የሰብአዊ እርዳታ ያስፈልገዋል፣ በዚህ ብቻ ሳይታጠር በተከሰተው ርእደ መሬት በሕዝብ ላይ ካስከተለው የሰብና የንብረት ጉዳይ ባሻገር ካስከተለበት የሥነ ልቦናዊ ጫና ለማቅለል የሥነ ልቦና ድጋፍ በጠቅላላ ቁሳዊ መንፈሳዊና ሥነ ልቦናዊ ድጋፍ ያስፈልገዋል። የወደመው የመገናኛ መሥመር የመኪና መንገድ፣ የመብራት ኃይልና የስልክ ግኑኝነት አገልግሎት መስጫ ሁሉ ጥገና ያስፈልገዋል። በካትማንዱ ብቻ ካንድ ሚሊዮን በላይ የሚገመት ሕዝብ አለ መጠለያ ቀርቷል፣ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ለተጎዳው ሕዝብ የተሟላ ድጋፍ እንዲያቀርብ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ በማቅረብ፣ በነፓል የሚገኘው የካሪታስ ቅንርጫፍ ለተጎዳው ሕዝብ የተሟላ ድጋፍ በማቅረቡ ረገድ እየተረባረበ መሆኑ ገልጠው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.