2015-04-24 16:06:00

ዓለም አቀፍ የአቢያተ ትምህርትና ተማሪዎች ግኑኝነት ማኅበር


ቅዱስ አባታችን ር.ሊጳ. ፍራንቸስኮ ማኅበራዊ ውህደትና ባህላዊ ግኑኝነት አማካኝነት ሰላም የተካነው ዓለም ለመገንባት በሚል ዓላማ ገና የቦኖስ አይረ ሊቀ ጳጳሳት እያሉ ያቋቋሙት ዓለም አቀፍ የአቢያተ ትምህርትና ተማሪዎች ግኑኝነት ማኅበር እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በቫቲካን ረዲዮ ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ የዚህ ማኀበር የላቲን አመሪካ ጉዳይ ወካይ የመላ ላቲን አማሪካ ትምህርት ቤቶችና ተማሪዎች ግኑኝነት ፈደራላዊ ማኅበር በላቲን አመሪካ ስለ ወጠናቸው እቅዶች በተመለከተ አጭር መግለጫ መስጠቱ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ ገለጡ።

ጳጳሳዊ የሥነ ማኅበራዊ ተቋም ዋና አስተዳዳሪ ብፁዕ አቡነ ሳንቸስ ሶሮንዶ የተወጠነው እቅድ በሕንጸት ዘረፍ አቢይ ግፊት ያለው እቅድ መሆኑ ገልጠው፣ በዚህ አጋጣሚም በእቅዱ ርእስ ዙሪያ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ውይይት መካሄዱና እሳቸውም እቅዱ ተቀባይነት ያለው መሆኑ እንዳሰመሩበት አስታውሰው፣ በቺለ ሊካሄድ በተወሰነው የላቲን አመሪካ ዋንጫ ግጥሚያ ወቅት እግብር ላይ የሚውል የትብብር እቅድ እንደወጠንና ይኽ በላቲን አመሪካ የሁሉም አቢያተ ትምህርትና ተማሪዎች ድራዊ ግኑኝነት በሚል መጠሪያ አንድ ብሎ ድኽነትና የግድ የለሽነት ባህል ለመዋጋት በተለያየ ምክንያት ከሕንጸት ባህል ተገሎ የሚኖር አንድም ወጣት እንዳይኖር ሕንጸት ለሁሉም በሚል አላማ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ገና በርጀንቲና ርእሰ ከተማ ቦኖስ አይረስ ሊቀ ጳጳሳት በነበሩበት ወቅት ያስጀመሩት ዓላማ መላ ዓለም ያቀፈው ማኅበር ሆኖ በዚህ ዘርፍ አቢይ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ መግለጣቸው ሎሞናኮ አመለከቱ።

የማኅበሩ እቅድ ከቀን ወደ ቀን ከፍ እያለ መሆኑና ይኽ ደግሞ በሕንጸት ዘርፍ ያለው ሰፊና ጥልቅ ዓላማ ያለው ተቀባይነት የሚያረጋግጥ ጉዳይ ነው። የዚህ ማኅበር ዓላማ ለማነቃቃት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከተለያዩ የስፖርት የባህል አካላት ጋር በመገናኘት በዓለም ማኅበራዊ ውህደትና ባህላዊ ግኑኝነት በማስፋፋት የምንኖርበት ዓለም ሰብአዊ ልክነት ያለው እንዲሆን የሚሰጡት ምዕዳን በዓለም የሚታዩት ግጭቶችና ጦርነቶች አቢይ ምክንያት የሕንጸትና የግኑኝነት የውይይት ባህል መጓደል በመሆኑም ጸረ ሰብአዊ የሆነው ተግባር ሁሉ በሕንጸትና በግኑኝነት ባህል አማካኝነት ለመቅረፍ ያለመ የማኅበሩ ዓላማ እግብ ለማድረስ የሚያግዝ እቅድ መወጠኑና እቅዱ በማስደገፍ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራችስኮ ውይይት እንደተደረገበት ማሳወቃቸው ሎሞናኮ ገለጡ።

የዚህ ዓለም አቀፍ ማኅበር እቅዶች እግብ ለማድረስ የእግር ኳስ ዓለም አቢይ አስተዋጽዖ እየሰጠ መሆኑ ሲገለጥ፣ በዚሁ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ አቢይ እውቅና ያላቸው የቀድሞ የአርጀንቲ ብሔራዊ ቡድን ተሰላፊ ዲየጎ ማራዶና ለመጥቀስ የሚቻል ሲሆን፣ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር በተካሄደው ግኑኝነትና በተሰጠው መግለጫም መሳተፋቸውና የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ደጋፊ የሰውን ልጅ ለማነጽ የሚያቀርቡት እቅድ ደጋፊና እግብ ለማድረስ ጥረት ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይሉ ገልጠው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የምንኖርበት ዓለም የሰላም የመግባባትን የመረጋጋት ሥፍራ ይሆን ዘንድ የሚሰጡት ምዕዳንና የሚያነቃቁት መርሃ ግብር ሁሉ በተቻላቸው አቅም በማነቃቃትና በመደገፍ በዚህ ዓላማ ተጠምደው ከማገልገል ወደ ኋላ እንደማይሉ ቃል ገብተው ሁሉም የስፖርት አካላት ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጎን ናቸው እንዳሉ ሎሞናኮ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.