2015-04-24 16:13:00

ብፁዕ ካርዲናል ኮማስትሪ፦ ቅዱስ ከፈን የእግዚአብሔር ፍቅር ለሰው ዘር የሚያወሳ ነው


እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 23 ቀን 2015 ዓ.ም. የሮማ ሰበካ የመናብርተ ጥበብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ቢሮና የሮማ መንፈሳዊ ንግደት ተግባር በመተባበር ያዘጋጁት እጅግ የበለጠው ፍቅር በሚል ርእስ ዙሪያ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ከፈን ማእከል ያደረገ  ዓውደ ጉባኤ ሮማ ሰበካ በሚገኘው በቅዱስ መስቀል ዘኢየሩሳሌም ባዚሊካ መካሄዱ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሪና ታማሮ ገለጡ።

ይኽ የተካሄደው ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. የመናብርተ ጥበብ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ከፈን በታቀበበት በቶሪኖ ሰበካ የሂያካሂዱት መንፈሳዊ ንግድ ምክንያት ያደረገ መሆኑ ሲገለጥ፣ ስለ ተካሄደው ዓውደ ጉባኤ በማስመልከት የቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ሊቀ ካህናት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ኮምስትሪ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ቅዱስ ከፈን ቀርቦ የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ስቃይና ሞት የላቀው ፍቅሩ ለማስተንተን የሚያመች የታደለ ቅዱስ ሥፍራ መሆኑ ገልጠው፣ በቅዱስ ከፈን ያለው ምስል የአንድ እጅግ የተሰቃየ ሰው ምልስ የታተመበት ቢሆንም ቅሉ፣ በውስጡ የፍቅር እርጋታ የሚታይበት ምስል ነው፣ ለምን እንዲህ ሆነ ብለን ለመጠየቅ አንችልም ምክንያቱም መልሱ በወንጌል የሚገኝ ግልጽ ነው። ስለ ፍቅር የተሰቃየ ነው። ቅዱስ ከፈን ስታይ የሚሰማህ የምታየው ፍጹም ፍቅር ነው። ቅዱስ ቻልረስ ደ ፉኩል በሰሃራ ምድረ በዳ እያለ ይዞት በነበረው ቅዱስ ከፈን ምስል ዘንድ እግዚአብሔር ይኽን ያክል አፍቅሮሃል የሚል ጽሑፍ ያሰፈረበት እንደነበር አስታውሰው፣ እግዚአብሔር ምንኛ እንዳፈቀረን የሚያረጋግጥልን፣ ባጠቃላይ የእግዚአብሔር የላቀው ፍቅር ለሰው ዘር የሚያወሳ ማንንም ያማያገል ኵላዊ የእግዚአብሔር ፍቅር የሚገልጥ ቅዱስ ምስል ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.