2015-04-20 16:25:00

የቅዱስ ከፈን ትርኢት በቶሪኖ


እ.ኤ.አ. እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2015 ዓ..ም. የሚዘለቀው በቶሪኒ ሰበካ ጥበቃ ሥር የታቀበው የቅዱስ ከፈን ትርኢት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ቶሪኒ በሚገኘው ካቴድራል የከተማይቱ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቸሳረ ኖስሊያ በሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በይፋ መከፈቱ ሲግለጥ፣ ብፁዕነታቸው ባሰሙት ስብከት ቅዱስ ከፈን የእግዚአብሔር ደግነት በሰብአዊው ሕይወታችን መገለጡ የሚያስታውሰን ተጨባጭ እውነት መሆኑ ገልጠው፣ የዚህ ትርኢት መሪ ቃል እጅግ ታላቅ

ፍቅር የተሰኘ መሆኑም አስታውሰው፣ በዚህ ቅዱስ ትርኢት ፊት ሁላችን ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር ሆነን እኛ ሳንሆን ያንን ቅዱስ ከፈን የምናየው በቅዱስ ከፍን ያለው ያ የእግዝአብሔር የምህረት ምስል እኛን እንደሚመለከተን እንመስከራለን፣ አሁንም በምንኖርበተ ዓለም እጅግ ስቃይና መከራ መኖሩንም ይገልጥልናል እንዳሉ ከቶሪኖ ሰበካ የተላለፈው መግለጫ ይጠቁማል።

ብፁዕ አቡነ ኖሲሊያ ከቅዳሴው ፍጻሜ በኋላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. በ 1998 ዓ.ም. ቅዱስ ከፈን በማስመለከት ባሰሙት ቃል በቅዱስ ከፈን ዙሪያ የሚከናወነው የሥነ ምርምርና የሥነ ታሪክ ጥናት የሚያገኘው መልስና የሚሰጠው ትንተና እውነት ወይንም ሃሰት ብላ ፍርድ ለመስጠት የእርሷ ኃላፊነት አይደለም፣ ነገር ግን አለ ምንም ቅድመ ፍርድ የሚሰጡት መልሶች በማጤን እንደምትመረምርና በቅዱስ ከፈን ዙሪያ የሚካሄዱት የሥነ ምርምርና የሥነ ታሪክ ጥናቶች ታበረታታለች ያሉትን ሃሳብ አስታውሰው፣ ቤተ ክርስቲያን በሚሰጡት የሥነ ምርምር መግለጫዎች ዙሪያ ሳትወሰንና ውድቅ ሳታደርግ አንዱም በማጋነን ተቀባይነት ያለው ነው ሳትልና ሳትወገን፣ ሆኖም ያ ቅዱስ ከፈን አራቱ ወንጌላውያን ከሚያወሱት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ ጋር የተጣመረና የሚመሳሰል ታሪክ መሆኑ ግምት የምትሰጥና ከዚህ አቢይ ምሥጢር ከሆነው ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይና ሞት ጋር የንድንገናኝ ያንን ለድህነታችን የተከፈለውን ዋጋ እንድናስተነትን የሚያበቃን ቅድስ  መሣሪያ መሆኑ ትገልጥልናለች፣ ተፈላጊው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ከፈን ነው ወይንም አይደለም ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ሳይሆን በዚያ ቅዱስ ከፈን ፊት ተኩኖ የሚስተነተነውና የሚንጸባረቀው እራስ አሳልፎ ከመስጠት የበለጠ ፍቅር እንደለሌ ለመዳናችን የተከፈለው መሥዋዕት ነው ብለዋል።

በመቀጠልም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የቅዱስ ከፈን የሥነ ምርምር ጉዳይ አስተዳዳሪ ጃን ማሪያ ዛኮነ ይላሉ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታዮች ሆነው ያለፉት አርእሰተ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ከፈን በተመለከተ በእምነትና በሥነ ምርምር መካከል ያለው ልዩነት አበክረው አስምረውበታል፣ ምክንያቱም ቅዱስ ከፈን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው አይደለም የሚለው ጥያቄ መልስ እምነት የሚመለከት ጉዳይ አይደለም፣ ቅዱስ ከፈን ለገዛ እራሱ ለተለያዩ ሥነ ምርምሮች ተጋርጦ መሆኑ በማብራራት፣ የቅዱስ ከፈን ታሪክ የምኅረት ትእምርና የአምልኰ ታሪክ ነው፣ ቅዱስ ከፈን የሚያቀርብልን ምስል የትስብእት የድህነት ታሪክ ነው። እኛን ለማዳን እግዚአብሔር ሰው ሆኖ በመካከላችን ተገኘ ስለ እኛ መዳን የከፈለው መሥዋዕት የሚያወሳ እግዚአብሔር ፍቅር መሆኑና ይኽ ፍቅር ደግሞ ገዛ እራስ አሳልፎ እስከ መስጠት የሚይበቃ መሆኑ በአራቱ ወንጌል የተገለጠው ታሪክ የሚያወሳ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃልዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.