2015-04-17 16:13:00

ብፁዕ አቡነ ኵወረብ፦ በነዲክቶስ 16 ትሁትና ጥልቅ የእግዚአብሔር አገልጋይ


ቅዱስነታችው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ገዳመ እመ ቤተ ክርስቲያን መኖር ከጀመሩ ይኸው ሁለት ዓመታችውን እንዳስቆጠሩ የሚታወስ ሲሆን፣ ሚያዝያ 16 ቀን የሚያከብሩት በዓለ ልደታቸው ምክንያት ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንዲሁም ከተለያዩ አበይት ብፁዓን

ካርዲናሎችና ሊቀ ጳጳሳት ካህናትና ከተለያዩ አበይት የመንግስት አካላት ጭምር መልእክት እየደረሳቸው መሆኑ ሲገለጥ፣ በነዲክቶስ 16ኛ ያከበሩት 88 ዓመት ዕድሜ ምክንያት በአሁኑ ወቅት የቅድስት መንበር የኤኮኖሚ ጉዳይ ዋና ጸሓፊ የበነዲክቶስ 16ኛ ሁለተኛ የግል ዋና ጸሓፊ በመሆን ያገለገሉት ብፁዕ ኣቡነ አልፍረድ ኵወረብ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፤ በነዲክቶስ 16ኛ ትሁትና ጥልቅ የእግዚአብሔር አገልጋይ በማለት ገልጠው፣ ለቅዱስነታቸው ልኅቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የነበራቸው ፍቅር ከፍ እያለ መምጣቱና በተለያየ አጋጣሚም ሲገናኙዋቸውም ጥልቅና የጠበቀ ሰላምታ እንደሚለዋወጡና በጸሎት እንደሚተሳስቡ የሚያረጋግጥ ሃሳብ እንደሚለዋወጡ ገልጠው፣ ምንም’ኳ የእድሜ መግፋት ቢታይባቸውም በእውነቱ አቢይ የሕይወት የትህትና የቲዮሎጊያ ትምህርት በቃልና በሕይወት አስተማሪ አሁንም እግዚአብሔር በፈቀደውና በጠራቸው ለየት ባለ መንገድ ተመሳሳይ አገልግሎት እየሰጡ ናቸው፣ ብዙ ሰዎች ምእመናን ለበነዲክቶስ 16ኛ ያላቸው ፍቅር ከቀን ወደ ቀን ከፍ እያለ መምጣቱ እንደሚመሰክሩላቸውም አስታውሰው፣ ጥልቅ አስተዋይ ሊቅ ጸላይ መንፍሳዊነት የተካኑ በእውነት ቀርበህ ስተገናኛቸው የሚስተዋል ሓቅ ነው ብለው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.