2015-04-17 16:02:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ ውይይት የማያውቅ ዝም ማሰኘት የሚሻ ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሌ ዘነግህ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በመቀጠል በዕለቱ ምንባብ ተንተርሰው፦ “ሓሳብ ለሓሳብ ለመለዋወጥ መወያየት የማያውቅ እግዚአብእሔርን አይታዘዝም፣ እግዚአብሔር ለሚለግሰው ለውጥና ህዳሴ የሚያበስሩትን ዝም ለማሰኘት የሚሻ ይሆናል” በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ ስብከት መለገሳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

የዕለቱ ሊጡርጊያ ስለ ተአዝዞ የሚናገር መሆኑ የገለጡት ቅዱስ አባታችን፦ “እግዚአብሔርን መታዘዝ መንገድን ለመለወጥ ብርታት፣ እኔ በወጠንኩትና በማውቀው መንገድ ለመጓዝ ሳይሆን ለየት ባለ መንገድ ለመጓዝ ለሚጠራው ቃል መታዘዝ ማለት ነው። መንገዳችንን እንድንለውጥ ለሚጠይቀው ጌታ ለመታዘዝ ጽናት ያስፈልጋል። የተአዝዞ ጽናት፣ ጌታን የሚታዘዝ ዘለአለማዊ ሕይወት ያገኛል ጌታን የማይታዘዝ የእግዝአብሔር መአት በእርሱ ላይ ይወርዳል” የተሰኘው ሃሳብ በዕለቱ ከግብረ ሐዋርያት ምዕ. 5 ከቁ. 27 – 33 ያለውን ምንባብ ጠቅሰው በማብራራት “ለሰው ከመታዘዝ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ይገባል…በማለት ሐዋርያት የኢየሱስ ስም በመጥራት እንዳያስተምሩ ወንጌልን እንዳያበስሩ የተጠሩ በዚህ አገልግሎት ምክንያትም በካህናትና በካህናት አለቆች ፊት ተከሰው ይቀርባሉ፣ ሐዋርያት ሲያበስሩ ሲፈውሱ ተአምር ሲፈጽሙ ወንጌል የሚከተል ሕዝብ ብዛት እያደገ በምጣቱ ምክንያት የሸንጐ አለቆች ካህናትና የካህናት አለቆች በቅናትና በምቀኝነት ተሞልተው፣ ለእስር ይዳርጓቸዋል፣ የእግዚአብሔር መልአክ ወንጌልን እንዲያበስሩ በሌሊት ከእስር ነጻ ያወጣቸዋል። ካህናትና የካህናት አለቆች ይኸንን ዳግም በማየት ይቆጣሉ ለምርመራም ያቆሙዋቸዋል፣ ጴጥሮስ ግን ለሰው ከመታዝዘል ለእግዚአብሔር መታዘዝ ይገባል ሲል ይመልስልቸዋል፣ ይኸንን የጴጥሮስ መልስ ካህናቱና የካህናት አለቆች ነን ባዮች ሳይገባቸው ይቀራል፣ ግራ ይጋባሉ፣ እነዚህ የሸንጐ አለቆች ካህናና ሊቀ ካህናት የሕግ ሊቃውንት የሕዝበ እስራኤል ቲዮሎጊያ እርሱም የእግዚአብሔር የመገለጥ ታሪክ አብጠርጥረው የሚያውቁ አስተማሪዎች ሆነው እያሉ የእግዚአብሔር ማዳን፣ የድህነት እቅድ ሳይገባቸው ይቀራል” ያሉት ቅዱስ አባታችን ለምን ይኽ ዓይነቱ ልብን የማደንደን ተግባር፣ ልበ ደንዳና አዎ የእነርሱ ልብ ደንዳናነት ሁሉን ለማወቅ ከሚሻ ስሜት የሚከሰት ሳይሆን ድርቅና የልብና የአእምሮ ድርቅና ሙላት የሚወልደው መሆኑ እንዳብራሩ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

መወያየት የማያውቅ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ያዳግተዋል። የልብና የአእምሮ ድርቀት በታሪክ የሚታይ ሁነት ነው። በገዛ እራስ መዘጋት ለመወያየት አለ መሻት፣ የሕግ ሊቃውንቱ ከእግዚአብሔር ጋር የማይወያዩ ናቸው። ምክንያቱም መጸለይን አያውቁምና፣ የጌታ ድምጽ ለማዳመጥ የማይተጉ፣ ከሌሎች ጋር መወያየትን የማያውቁ፣ የሕግ ተንታኞች በታሪክ ጌታ ለሚስጠው ምልክት የታወሩ፣ በገዛ እራሳቸው በሕዝባቸውና ለሕዝባቸው የተዘጉ፣ ይኽ ልበ ደንዳናነት እግዚአብሔርን ላለ መታዘዝ ይዳርጋቸዋል። የእስራኤል የሕግ ሊቃውንት የሕዝበ እግዚአብሔር ቲዮሎጊያ ሊቃውንት ትንግርት ማዳመጥ መወያየት አለ ማወቅ ነው። ውይይት ከእግዚአብሔርና ከወንድሞች ጋር፣ አነርሱ ግን ይኸንን የማያወቁ ናቸው” ያሉት ቅዱስ አባታችን “የማይወያይ መወያየትን የማያውቅ የእግዚአብእሔር ህዳሴን የሚያበስሩትን ዝም ለማሰኘት የሚሻ ይሆናል። እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚገልጠው ምልክት ሁሉ ለማወቅ የማይችል ይሆናል፣ ሌሎችን ዝም ለማሰኘት በንዴት ይነሣሣል፣ ክርስቶስ ከሞት ተነሣ የሚለው አዲስነት ዝም ለማሰኘት ይቃጣቸዋል፣ ልክ እንደ የጌታ መቃብር ዘብ ጠባቂዎች መነሣቱን ከማመን ይልቅ ደቀ መዛሙርት መጥተው ከመቃብር ሰረቁት ብሎ ለማመን ይቀላቸዋል፣ ለእግዚአብሔር ድምጽ መዘጋት ማለት እንዲህ ነው። በዚህ መሥዋዕተ ቅዳሴ ለመምህራን ለሕግ ሊቃውንት ሕዝበ እግዚአብሔር በገዛ እራሱ እንዳይዘጋ ከሌሎች ጋር እንዲወያዩ ከጌታ ጋርና ከወንድሞች ጋር እንዲወያዩ ያስተምሩ ዘንድ እንጸልይ፣ ከጌታ ቁጣ ለመዳን የሚችሉትም እንዲህ ባለ መንገድ ነው” ብለው የለገሱት አስተንትኖ እንዳጠዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.