2015-04-15 16:38:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. እስከ ወርሃ ሰኔ የሚያከናውኗቸው የፍጻሜዎች መርሃ ዕለት


ጳጳሳዊ የሊጡርጊያ ክብረ በዓላት መምህር ብፁዕ አቡነ ጉይዶ ማሪኒ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 14 ቀን 2015 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. በወርሃ ሰኔ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሠራኢነት የሚከናወኑት ክብረ በዓላትና ፍጻሜዎች ዝርዝር የተኖረበት መርሃ ዕለት በይፋ ማቅረባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ ዘጠኝ ሰዓት ተኩል በሚመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ የክህነት ማእርግ ይሰጣሉ። እ.ኤ.አ. ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓ.ም. በሮማ አቅራቢያ ኦስቲያ ከተማ በሚገኘው በንግስተ ሰላም ቁምስና ሐውጾተ ኖልዎ ያከናውናሉ። እ.ኤ.አ. ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ የሚያካሂደው ጠቅላይ ጉባኤ መክፈቻ ምክንያት በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ ልክ አምስት ሰዓት ተኩል መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚመሩ ብፁዕ አቡነ ማሪኒ አስታውቀዋል።

እ.ኤ.አ. እሁድ ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ አስር ሰዓት ለጆቫና ኤሚሊያ ደ ቪለኑወቭ፣ ለማሪያ ክርስቲና ዘንጽሕት ድንግል ማሪያም ብራንዶ፣ ለማርያ አልፎንሲና ዳኒል ጋታስ፣ ለማሪያ ዘስቁል ኢየሱስ ቡርድይ ቅድስና ለማወጅ የሚያርገው መሥዋዕተ ቅዳሴ ይመራሉ። ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም. በዓለ ጰራቅሊጦስ ምክንያት በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ከጠዋቱ ልክ 10 ሰዓት ላይ መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚመሩ የገለጡት ብፁዕ አቡነ ማሪኒ አክለው ሰኔ 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ዓመታዊ በዓለ ሥጋሁ ወደ ደሙ ዘእግዚእነ ምክንያት በአጸደ ቅዱስ ዮሓንስ ዘላተራኖ መሥዋዕተ ቅድሴ መረተው እንዳበቁ እስከ ቅድስት ድንግል ማርያም ማጆረ በቅዱስ ቁርባን የሚመራ ዑደት መርተው ጸሎት ቡራኬው እንዳበቃም ቅዱስ ቁርባናዊ ቡራኬ ይሰጣሉ። ቅዳሜ ሰኔ 6 ቀን 2015 ዓ.ም. በሳራየቮ ለዓለም አቀፋፍ ሐዋርያዊ ዑደት ይነሳሉ፣ እ.ኤ.አ. ከሰኔ 21 ቀን እስከ ሰኔ 22 ቀን 2015 ዓ.ም. በኢጣሊያ ቶሪኖ ከተማ ሐውጾተ ኖልዎ ያካሂዳሉ። ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. የቅድስና አዋጅ ምክንያት የጠሩት የብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ ይመራሉ። ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የቅዱሳት ጴጥሮስ ዎጳውሎስ ዓመታዊ በዓል ምክንያት መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው፣ ለሁሉም አዳዲስ ጴጥሮፖሊታ  አክሚም ባርከው እንደሚለግሱም አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.