2015-04-15 16:32:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ጥሪ ከገዛ እራስ ወጥቶ ጸአት ወደ እግዚአብሔርና ወደ ድኾች ማለት ነው


እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚከበረው 52ኛው ዓለም አቀፍ ስለ ጥሪ የጸሎት ቀን ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቤተ ክርስቲያን ወንጌላዊ ተልእኮና አስፍሆተ ወንጌል ተግባር ማእከል ያደረገ መልእክት ማስተላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ስተፋኖ ለዝይኒስኪ ገልጠው፣

ጥሪ ከገዛ እራስ ወጥቶ ወደ እግዚአብሔርና ወደ ድኾች መሰደድ ማለት መሆኑ ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት ተንትነው፦ “ጥሪ ጸአት ነው፣ እርሱም ጸአት ወደ እግዚአብሔርና ወደ ድኾች ማለት ነው። ጸአት መሠረታዊ የጥሪ ገጠመኝ ነው። የክርስቲያን ጥሪ ከአንድ ጥልቅ ወንጌላዊ ልኡክነት ገጠመኝ የሚወለድ ነው። ይኽ የሚቻለውም ደግሞ ከገዛ እራስ ወጥቶ እውነተኛና ትክክለኛ ጸአት ከዚያ በቅዱስ መጽሐፍ ሕዝበ እግዚአብሔር በክርስቶስ አዲስ ሕይወት ለማግኘት ከባርነት ለመላቀቅ ከፈጸመው ጸአት ጋር የሚገናኝ ሲሆንና፣ ከድህነት ታሪክና ከክርስትና እምነት ካለው ንቁ ታታሪነት ጋር በማጣመር የሚኖርም ነው” በማለት አብራርተው የዚያ የጸአት እንቅስቃሴና ሂደቱ የጥሪ ትርጉም ሲሆን፣ የግል ጥሪ የሚመለከት ብቻ ሳይሆን የመላይቱ ቤተ ክርስቲያን የወንጌላዊ ልኡክነትና አስፍሆተ ወንጌል ተግባር የሚመለከት ነው” ብለው ወንጌል የምታበስር ቤት ክርስቲያን ከሰው ጋር ለመገናኘት ከገዛ እራሷ በመውጣት የወንጌል ነጻ አውጪው ቃል ታበስራለች፣ በጌታ ጸጋ አማካኝነትም የቆሰለውን አካልና ነፈስ ትፈውሳለች፣ ድኾችንና በድኽነት ጫንቃ ስር የሚገኙትን ከወደቁበት ታነሳለች ሸክማቸውን ታቀላለች” ክርስቲያናዊ ጥሪ በምድር የእግዚአብሔር መንግሥት ለመገንባት ተጨባጭ አገልግሎትና በግብረ ሠናይ የተካነ በተለይ ደግሞ ለድኾች ማገልገል ማለት መሆኑ ባስተላለፉት መልእክት አሳስበው ከዚህ ጋር በማያያዝም ለወጣት ትውልድ ያቀና ጥሪ ሲያቀርቡ፦ በምንኖርበት ዓለም የወጣት ትውልድ ቅን ፍላጎትና እቀድ የሚያደበዝዝ ወጥመድ አንዳለ አስታውሰው፦ “የጥሪ አብነትና አርአያ የሆነቸውን የዚያች አለ ምንም ፍርሃት እነሆኝ እንዳልከው ይሁንልኝ ስትል ለጌታ ጥሪ ሙሉ መልስ እንደሰጠችው ቅድስት ድንግል ማርያም የኢየሱስ ክርስቶስ ዱካን በመከተል ለመራመድ ካለ ምንም ፍርሃት  ከገዛ እራስ ለመውጣት አትፍሩ” በማለት ያሰተላለፉት መልእክት እንዳጠቃለሉ ማስተላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ስተፋኖ ለዝይኒስኪ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.