2015-04-13 15:30:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ሕያው ምስክሮች እንጂ አስተማሪዎች ብቻ አትሁኑ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የውፉያን ዓመት ምክንያት በማድረግ ባለፉት ቀናት በሮማ ከተማ የውፉያን ማኅበርና ገዳማት የዘርአ ክህነት ተማሪዎች አለቆች ዓውደ ጉባኤ 1 ሺሕ 400 ተሳታፍያንን  እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 11 ቀን 2015 ዓ.ም. አገረ ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ አስታወቁ።

ቅዱስ አባታችን በለገሱት ምዕዳን በዚህ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ብዛት መጓደል በሚታይበት በአሁኑ ወቅት፣ እያንዳንዱ የዘርአ ክህነት አስተማሪ በወጣት ልብ የኢየሱስ ክርስቶስ ልብ ይቀርጽ ዘንድና ይኽ ደግሞ የክርስቶስ ስሜት የሆነውን ሁሉ በውስጣቸው ለማኖር የሚያበቃ መሆኑ አሳስበው፣ በየዘርአ ክህነት አስተማሪ የውፉይ ሕይወት ውበትና ውህበት በቃልና በሕይወት በሚመሰክርበት ሥፍራ የዘርአ ክህነ ተማሪዎች እጥረት አይኖርም፦ “አፍሪ ምስክርነት መኖር አለበት፣ ፍሪያማ ምስክርነት ሳይኖር ሲቀር፣ ቃልና ሕይወት ያጣመረ ምስክርነት በሌለበት ሥፍራ ሁሉ ጥሪ ይኖራል ለማለት ያዳግታል፣ ስለዚህ እያንዳንዱ የዘርአ ክህነት አስተማሪ ለአስተማሪነት ሳይሆን ለሕያው ምስክርነት የተጠራ ነው። የዘርአ ክህነት አስተማሪ ተልእኮም እርሱ ነው። አስተማሪዎች ብቻ ሳትሆኑ የተቀበላችሁት መንፍሳዊ የማኅበራችሁ መርሆ በወንጌላዊ ሕይወት አማካኝነት በቃልና በሕይወት መሳክሪያን ለመሆን የተጠራችሁ ናቸሁ” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋኒ አክለው፣ በእያንዳንዷ ቀንና ሰዓት በክህነት ጥሪ የክርስቶስ ተከታይነት ያለው ኃሴት በኃሴት በመኖር ሲመሰከር እውነተኛ ምስክርነት ለማቅረብ የማያዳግትም መሆኑ አብራርተው ይኽ ደግሞ ከክርስቶስ ጋር ያላቸው የግል ግኑኝነትና ጥብቅ ወዳጅነት እንደ ቅድመ ሁኔት የሚጠየቀው መፍነሳዊነት መሆኑ እንዳሰመሩበት ገልጠዋል።

እያንዳንዱ የዘርአ ክህነት አስተማሪ ያች ከጌታ ጋር የግላዊ ግኑኝነት ጸጋ የታደለባት ቀን ተዘርክሮ ብዙውን ጊዜ በተለያየ የአገልግሎትና መርሃ ግብርና ውጣ ውረድ የሚዘነጋው ገጠመኝ ዕለት በዕለት የሚከበር መሆን አለበት፣ እውነተኛው ምስክርነት ለማቅረብ ያችን ከጌታ ጋር ጥብቅ ግኑኝነት የታደለባት ቀን መለስ ብሎ ማክበር ያስፈልጋል። ይኽ የተዘክሮ በዓል የማይከበር ከሆነ ተዘክሮ ከሌለ የክህነት ጥሪ ለምን እንደሚኖር ይዘነጋል፣ ትርጉሙም ለመረዳት ያዳግታል” እንዳሉ ቸንቶፋንቲ ገልጠዋል።

የውፉይ ሕይወት ጥሪ የቤተ ክርስቲያን አቢይ ሃብት ነው። በመሆኑም የዘርአ ክህነት አስተማሪ መሆን ይኸንን እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያኑ ያደላት የላቀው ሃብት በሚገባ ማስተዳዳር ማለት ነው። ስለዚህ እንደ ሸክም ሳይሆን ጸጋ ነው። ወንጌላዊ ተልእኮና ልኡከ ወንጌል አስፈላጊ ነው፣ ሆኖም ግን ለወንጌላዊ ልኡክነት ማሰናዳት እጅግ አስፈላጊ ነው። ወንጌልን የማበሰር ፍቅር መዝራት፣ ለዚህ ፍቅር ማነጽ ለሁሉም በተለይ ደግሞ በጥጋ ጥግ የከተሞቻችንና የህልውና ክፍል ለሚገኙት ሁሉ ፍቅር መመስከር ወሳኝ ነው፣ ክርስቶስ ለተናቁት ለተናንሽ ለተረሱት የማበሰሩ ጥሪ በፍቅር በመኖር መመስከር አቢይ ተልእኮ ብቻ ሳይሆን አቢይ ኃላፊነትና የጥሪ ምክንያት ነው። በመሆኑም ይኽ ጥሪ ጽኑ መሠረት ይጠይቃል፣ ቤተ ሰብ በዚህ ዘርፍ አቢይ ሚና አለው” እንዳሉ የገለጡት ቸንቶፋንቲ እክለው አንድ የዘርአ ክህነት አስተማሪ ሊኖረው የሚገባው የላቀው ችሎታና ብቃት ለወጣት ትውልድ ክፍትና አቢይ ልብ ያለው፣ በምኅረት የተካነ ሁሉን በትህትናና በፍቅር የመቀበልና አለ ምንም ቁጠባ ሁለመናው ለዚህ ትውልድ አገልግሎት ማቅረ የሚል መሆኑ ያብራሩት ቅዱስ አባታችን፦ “ብዙውን ጊዜ ወጣት ትውልድ የማይለግስ ለእኔ የሚል የላቀውን ጉዳይ ለመምረጥ የሚሳነው ነው ተብሎ እንደሚገለጠው አይደለም፣ ስለዚህ ከመቀበል መለገስ የላቀ መሆኑ (ግብ. ሓዋ. 20.35) የሚመሰክርለት አካል ያስፈልገዋል። ይኽ ደግሞ የጥልቅ ነጻነት መሠረት ነው። በተአዝዞ ያለው ነጻነት በድንግል ልብ ያለው ለጋስነት በድኽነት ያለው ሃብት ለመመስከር ያበቃል። ወጣት ትውልድ በብቃትና በተሟላ ሁኔታ ማነጽ ያስፈልጋል”  ወጣት ትውልድ እነዚያ መላ ሕይወታቸውን ለእግዚአብሔር ያወከፉ በእድሜ የገፉት ካህናትና ገዳማውያን በመመልከት አስመሳይነት ከወዲሁ የመገንዘብ ብቃት ያለው ወጣት ከእነዚህ አዛውንት ካህናት የሚንጸባረቀው እውነተኛው ምስክርነት የማስተዋል ብቃት ያለው በመሆኑም፣ በእውነተኛ ምስክሮች የሚማረክ ነው። የዘርአ ክህነት አስተማሪዎች በጥሪ ማነስ ሳይደናገጡና ተስፋ ሳይቆርጡ የውፉይ ሕይወት ውበትና ውህበት በመመስከር ወጣት ትውልድ በኢየሱስ እንዲማረክ መጸለይ….አደራ የዘርአ ክህነት አስተማሪዎች ጸላያን ይሁኑ፣ ያሉት ቅዱስ አባታችን ስለ እኔ ጸልዩ፣ ምክንያቱም የጌታ ትዕግስት ያስፈልገኛ ብለው ያስደመጡት ምዕዳን ማጠቃለላቸው ቸንቶፋንቲ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.