2015-04-08 16:08:00

ሩዋንዳ፦ ዝክረ 21ኛው ዓመት የዘር ፍጅት፣ ተዘክሮና ይቅር መባባል


እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 7 ቀን 1994 ዓ.ም. በሩዋንዳ የተከሰተው ጅምላዊ ጭፍጨፋና የአገሪቱ መቅሰፍት ተብሎ የሚነገርለት በመቶ ቀናት ውስጥ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 6 ቀን 1994 ዓ.ም. የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ጁቨና ሃብያሪማና ይጓዙበት የነበረው አይሮፕላን ላይ በተጣለው ጥቃት ሳቢያ ከብሩንዲ ርእሰ ብሔር አቻቸው ጋር በመጓዝ ላይ እያሉ መገደላቸው ምክንያት የሁቱ ጎሳዎች ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚገመቱት የቱዚ ጎሳ አባላት ለሞት የዳረጉበት ዝክረ ዕለት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 7 ቀን 2015 ዓ.ም. መከናወኑ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ ሳባቲነሊ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።

በቱዚ ላይ የተፈጸመው ጅምላዊ መቅሰፍት በአፍሪቃ ታሪክ እጅግ አሰቃቂ ምዕራፍ ተብሎ የሚነገርለት ሲሆን፣ እጅ አለባቸው በሚባሉት ላይ ፍርድ የሚበይነው በታንዛኒያ ርእሰ ከተማ አሩሻ ልዩ የአለም ዓቀፍ ፍርድ ቤት ቢቋቋምም አሁንም ገና በጅምላዊ ቅትለት እጅ አለባቸው የሚባሉት ተጠያቂዎች በነጻነት እየኖሩ መሆናቸው የገለጡት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ መጠይቅ ያካሄዱት ጅምላዊ እልቂት በተጣለበት ዓመት የ 10 ዓመት እድሜ የነበሩት ከነቤተሰባቸው ጋር ተሰደው በኢጣሊያ መኖር ከጀመሩ 10 አመት ያቆጠሩት የሩዋንዳ ተወላጅ የመንበረ ጥበብ ተማሪ በቫቲካን ቤተ መዘክር ሠራተኛ ቫለንስ ሙሳብየሙንጉ ገልጠው፣ የሩዋንዳ ርእሰ ብሔር ይበሩበት የነበረው አይሮፕላን እንደተመታና የርእሰ ብሔሩ መገደል እንደተሰማ ወዲያውኑ የሁቱ ጎሳዎች የቱዚ ጎሳ መኖሪያ ቤት በእሳት ማጋየት ጀምረው፣ ጉዳዩ እየከረረ ሲመጣ ከሞት አደጋ ለማለጥ የቱዚ ጎሳዎች በተለያዩ ቁምሳናዎች ሲደበቁ ገሚሶቹም ወደ ጎረቤት አገሮች ለመሰደ መገደዳቸው አስታውሰው፣ ወላጅ አባታችን ይጣል በነበረው ጥቃት ሳቢያ መገደላቸውና በጠቅላላ የቱዚ ጉሳ አባላት ዕለታዊ ሕይወት እጅግ ለአደጋ እየተጋለጠ የዚህ ጎሳ አባል የሆነው ሁሉ እንደ  ሲታደን የታየበት አሰቃቂ የአፍሪቃ ታሪክ ነው፣ በእውነቱ አንድ ሰው እንዴት አምሳያው በሆነው ሰው ላይ የዚህ ዓይነት አሰቃቂ የግድያ ተግባር ይፈጽማል የሚል ጥያቄ አሁንም ቢሆን ከአእምሮአቸው እንዳልተለያቸው ገልጠዋል።

ይኽ አሰቃቂው የሕይወት ምዕራፍ በማስታወስ መጻኢ ለማስተካከል እንጂ በዚያ ምዕራፍ ተቀምጦና ተክዞ ለመኖርም ሆነ ለብቃላ ገዛ እራሳ ማሰናዳት መልስ አይደለም፣ ያንን የተፈጸመው ዕልቂት ዛሬ በማስታወስ ይቅር ተባብሎ ሁሉም አለ ምንም የጥላቻ መንፈስ በጋራ ለመኖር የሚችልበት ሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮ ማረጋገጥ ያስፈላጋል፣ ይኽ ደግሞ በሩዋንዳ እየታየ ነው ብለዋል።

ከግጭቱ በፊት በሩዋንዳ ይደረገ የነበረው ከዜግነት መለያው ጎን የየትኛው ጎሳ አባል መሆንህ የሚገልጥ  በመታወቂያ ወረቀት ይሰፍር የነበረው ቀርቶ ሁሉም ሩዋንዳዊ መሆኑ ብቻ ይገለጣል፣ በትምህርት ቤት ጭምር የሚሰጠው ሕንጸት ሰላም ላይ ያቀና ተዘከሮ መቼም ቢሆን ይቅር በመባባል መንፈስ የተመራ መሆን እንዳለበት የሚያበክር  ነው ብለው ዛሬ ሰላማዊ የጋራ ኑሮ መሠረት ይዘዋል። ሰላም ለአገር አንድነት መሠረታዊ ኃይል መሆኑ ገልጠው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.