2015-04-06 15:40:00

ዓርብ ስቅለት፦ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ግብረ ሰናይ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ህማማት ሳምንት ሁሌ በየዓመቱ እንድሚያደርግቱ ይኸው ዘንድሮ በኮሎሰዮ አደባባይ ዓርብ ስቅለት ፍኖተ መስቀል በመሩበት ዕለት በሮማ ከተማ ለሚኖሩት ጎዳና ተዳዳሪ ዜጎች ሰብአዊና ቁሳዊ ድጋፍ በጳጳሳዊ ቤተ ምጽዋት ተጠሪ ብፅዕ አቡነ ኮንራድ ክራጀውስኪና ዋና ጸሓፍያቸው ብፅዕ አቡነ ዲየጎ ራቨሊ አማካኝነት መለገሳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

የመላ ዓለም ዓይኖች ቅድስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍርንቸስኮ ወደ መሩት የኮሎሰዮ ፍኖተ መስቅል ላይ ባተኮረበት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ኮለሰዮ በብርሃን ቦግ ባለበት ምሽት በሮማ ከተማ ብርሃን ቦግ በማይልበት ክልል ተነጥለው የሚኖሩ ዜጎች እንዳሉ የሚያስታውስ ሕይወት የሚኖሩ፣ እነዚህ ወቅታዊው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማት በማለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ደጋግመው የሚገልጡዋቸው የኅብረሰብ ክፍል መልካም የፋሲካ በዓል ምክንያት ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የተላከላቸው የሰብአዊና ቁሳዊ ድጋፍ እንደደረሳቸው ብፁዕእ አቡነ ክራጀውስኪ ገልጠዋል።

ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እርዳታው የደረሳቸው ሁሉ እግዚአብሔር በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አሳቢነት ዘወትር የሚደደርሳቸው ፍቅር ጥልቅ መሆኑ በመመስከር ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መልካም ፋሲካ መመኘታቸው ገልጠው። የመስቀል መንገድ ድኾች በሚገኙበት ጎዳና በመሄድ በተጨባጭ ሁኔታ ከሚኖሩት ጋር እንዲኖር ቅዱስ አባታችን ካለ መታከት የሚያቀርቡት ጥሪ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ራቨሊ አስታውቀዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.