2015-04-06 15:37:00

ብፁዕ አቡነ ዙፒ፦ ጸረ ክርስቲያን አመጽ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 3 ቀን 2015 ዓ.ም. በሮማ ኮሎሰዮ አደባባይ በመሩት ፍኖተ መስቀል በብዙ ሺሕ በሚገመቱት ማኅበረ ክርስቲያን ላይ የሚፈጸመው ቅትለት እያየ እንዳላየ ሆኖ የመኖር ምርጫ ያወገዘ እንደነበር ሲገለጥ፣ ይኽ ዓይነቱ ዝምታ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ግዴለሽነት መሆኑና ዝም ብሎ ማየት በሚፈጸመው ግፍና በደል እጅ እንዲኖርህ የሚያደርግ ነው በማለት እንዳወገዙት የሮማ ሰበካ ኅይተ ረዳት ብፁዕ አቡነ ማተዮ ዙፒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ ዘንድ የእነዚያ በአሁኑ ወቅት በእምነታቸው ምክንያት ለሞት ለስደት የሚዳረጉት ማኅበረ ክርስቲያን ሞትና ስቃይ ያለው ሱታፌ ብቻ የሚያሳስብ ሳይሆን፣ የእነዚህ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ስቃይና መከራ በተለያዩ መልኩ እየሰማን እንዳልሰማን እያየን እንዳላየን ሆነን የምንኖረው ግዴለሽነት በተባባሪነት የሚያስጠይቀቅ መሆኑን አለ ምንም ማመንታት ያሳሰበ እንደነበር ገልጠው፣ የዚህ ዓይነት በተባባርነት የሚያስጠይቅ ተግባር እንዳንከሰስ አደራ ሲሉ፣ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. የእምነት ሰማዕት አባ አንድረያ ሳንቶሮ አስታውሰው፣ “የማዳን ብቃት እንዲኖረን የሚያደርግ ስለ ሊሎች ገዛ እራስ አሳልፎ መስጠት ነው” ይኽ ደግሞ የሌላው ችግር ስቃይ መከራ ድኽነት እርሃብ በጠቅላላ እየሱስ እንዳደረገው ተካፋይ ሆኖ መኖር አማራጭ የሌለው ክርስቲያናዊ ጥሪ  መሆኑ አንዳሰመሩበት ገልጠው የሌላው ስቃይና መከራ አይመለከተኝም ብሎ ማለፉ ለገዛ እራሱ ለስቃይና ለሞት ከሚዳርጉት ሰዎች መተባበርና እኩል የሚያስጠይቅ ተግባር መሆኑ ነው ያብራሩት ብለዋል።

በተለያየ የዓለማችን ክልል ለስደትና ለስቃይ የሚደረጉት ክርስቲያኖች ሁኔታ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በኃላፊነት የሚያስጠይቅ ጉዳይ ነው። በፓኪስታን ኢራቅ በተለያዩ አገሮች በቅርቡ በኬንያ ጭምር በክርስቲያኖች ላይ የተፈጸመው ቅትለት በሶማሊያ ያለው ሁኔታ ባጠቃላይ ከዓለም አቀፍ ማኅበርሰብ አስቸኳይ መልስ የሚጠይቅ ሁነት ነው። ሰላም ለማረጋገጥ የእያንዳንዳችን በተለይ ደግሞ የዓለም አቀፍ መንግሥታት ኃላፊነት አቢይ ነው ብለዋል።

የሚሰቃዩትን አቢያተ ክርስቲያን እርዳ የተሰየመው ማኅበር በወር 322 ክርስቲያኖች ለሞት እንደሚዳረጉ ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ሲቻል፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወንጌላዊ ኃሴት በተሰየመው ሐዋርያዊ መልእክት አማካኝነት እንዳመለከቱትና ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. በ 1986 ዓ.ም. በአሲዚ በሁሉም በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል በየዓመቱ እንዲካሄድ ያነቃቁት ይኽ በዓለም ሰላም ለማስፋፋት በሚል ዓላማ ያነቃቁት የጋራ ጸሎትና ውይይት መርሃ ግብር የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበርሰብ መርህ በማድረግ በሁሉም አገሮች እያስፋፋው ያለው የመቀራረብና የመወያየት ባህል መሠረት በማድረግ የአሲዚ መፈስስ በማስፋፋት ረገድ የሚሰጠው አገልግሎት በስፋት ገልጠዉታል፣ ቤተ ክርስቲያን ግኑኝነትና የጋራ ውይይት ስትል አሸባሪያንና አክራሪያን ጸረ ሰብአዊ ተግባር ሲመርጡ ይታያል፣ ሆኖም ይኽ እነርሱ የሚከተሉት መንገድ የተነቃቃው የውይይት መንገድ ሊያዳክም አይገባም፣ ስለዚህ ጥርስ በጥርስ የሚለው የጥላቻና የግጭት ባህል መከተል አይገባም። የግኑኝነት የውይይት ድልድይ መገንባት ያስፈልጋል፣ ማኅበረ ክርስቲያን ይኸንን ድልድይ ለመገንባት የተጠራ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ካለ መሰልቸት ዘወትር ያሳስባሉ፣ በህማማት በበዓለ ፋሲካ ጭምር ደግመው አደራ በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.