2015-03-27 14:27:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ኃሴት የሚያጎናጽፈው በራዳው የእምነት ሕግ ሳይሆን በኢየሱስ ማመን ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ዘወትር ማለዳ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በመቀጠል እ.ኤ.አ. መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ኃሴት የሚያጎናጽፈው በራዳው የእምነት ሕግ ሳይሆን በኢየሱስ ማመን ነው በሚል ቅዉም ሃሳብ ዙሪያ አስተንትኖ መለገሳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን በላቲን ግጻዌ መሠረት ከኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 17 ከቁጥር 3-9 የተነበበው አንደውኛው ምንባብ ላይ በማተኮር፣ እግዚአብሔር ቃል እንደገባው መሠረት አብርሃም የታደለው አባት የመሆን ተስፋ ምክንያት በደስታ ይሞላል። አብርሃም እንደ ሚስቱ ሳራ በእድሜ የገፋ አዛውንት ሆኖ እያለ እግዚአብሔር ለገባለት ቃል አሜን አለ፣ ልቡ ለተስፋ ከፈተ፣ በዚህ ምክንያትም ሙሉ መጽናናት ታደለ። ኢየሱስ ለሕግ መምህራን “አብርሃም በተስፋ ነው ኃሴት የተሞላው፣ የሕግ መምህራን ሊቃውንት የተገባው የኃሴት ቃል ኪዳን ሊረዱት አልቻሉም፣ ተስፋ የሚወልደው ኃሴት ለመገንዘብ የተሳናቸው፣ ምክንያቱም መደሰትን አያውቁምና። ደስታ የሚሰጠው እምነት ነው፣ አባታችን አብርሃም ደስተኛ ለመሆን የበቃው እምነት ስለ ነበረው ነው። በእምነቱ ምክንያት ነው ጻድቅ የሆነው፣ የሕግ ሊቃውንቱ እምነትን ያጠፉ፣ የሕግ ሊቃውንት አለ እምነት። እንዳውም የሕግ ማእከል ትርጉም ጨረሰው የዘነጉ። የሕግ ማእከል ፍቅር ነው። እርሱም ፍቅር ለእግዚአብሔር ፍቅር ለባለንጀራህ የሚል ነው” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

የሕጉ ሊቃውንትና መምህራን የእምነት ስፍር ቁጥር የሌለው ሕግ የነበራቸው ሁሉ ሕጉን ያከብር ዘንድ የሚያዙ፣ እምነት ያልነበራቸው፣ እውነተኛውና የሕጉ መሠረታዊ ትርጉሙን ያላወቁ፣ እምነታቸውን በሕግ ላይ ያኖር፣ ሕግ ላይ የሙጥኝ ያሉ፣ የማይራመዱ፣ ግብር ለቄሳር መክፈል ወይንም አለ መክፈል፣ ይህች ሴት ሰባት ጊዜ ተድራለች ስለዚህ መንግሥተ ሰማይት ትገባለችን? በተሰኙት ጥያቄዎች የተጠመዱ፣ እዎ የእነርሱ ዓለምና ሕይወት ይኽንን ይመስል ነበር፣ የሕጎችን ጥልቅ ርጉሙ ሳይረዳቸው ውጫዊው ሁነቱን ማብጠርጠር የሚያወቁ፣ የእነርሱ አለም አለ እምነት አለ ፍቅር አለ እግዚአብሔርም ነው። ስለዚህም ነው ደስተኞች ለመሆን የተሳናቸው በማለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሕግ ሊቃውንት ማንነት ገልጠው፣ እነዚህ የሕግ ሊቃውንት በተለያየ ጊዜ ማሳለፊያ የሚዘናጉ ቢሆኑም ደስታው ግን ፈጽሞ ያልነበራቸው መሆናቸውንም ተንትነው፣ በፍርሃት የሚኖሩ፣ ይኽ ደግሞ አለ እግዚአብሔርና አለ እምነት በእግዚአብሔር አለ ምንም ተስፋ በእግዚአብሔር የሚኖር ሕይወት ገጠመኝ ነው፣ ልባቸው ድንጋያማ፣ የተከዙ አለ እምነትና አለ ተስፋ አማኝ መሆን እንዴት ይቻላል፣ እምነት አለ ደስታ የለም፣ እምነት ሳይኖር ሲቀር አልቦ ተስፋ ሲኮን አለ እውነተኛው ሕግ ሲኖር፣ አሳዳጅ ይኮናል፣ በራዳ የእምነት ሕግ ብቻ መኖርን ይመረጣል፣ የእምነት ደስታ፣ ወንጌላዊ ኃሴት የአንድ አማኝ እምነት መግለጫ ነው። አለ ኃሴት እውነተኛ እምነት አይኖርም፣ አብረን ኢየሱስ ያለው እርሱም ‘አብርሃም ይህች ሰዓት ለማየት በነበረው ተስፋ ኃሴት ተሞላ፣ ያንን ቀን በተስፋ ተመለከተ፣ ሙሉ ደስታም ታደለ፣ በተስፋ ደስተኞች እንሆን ዘንድ ጌታን እንጠይቀው፣ ያንን ከኢየሱስ ጋር ፊት የምንገናኝበት ቀን በተስፋ በመመልከት ደስታ የተሞላን እንሆን ዘንድ ጌታ ጸጋውን እንለምነው” በማለት የለገሱት አስተንትኖ እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.