2015-03-26 15:53:00

150 ሰዎችን አሳፍሮ ይበር የነበረ አንድ የጀርመን አይሮፕላን በደቡባዊ ፈረንሳይ ወድቀዋል


150 ሰዎችን አሳፍሮ ከእስጳኛ ባርቸሎና ከተማ ወደ ጀርመን ይበር የነበረ አንድ የጀርመን  አይሮፕላን   በደቡባዊ  ፈረንሳይ ላይ መውደቁ ታውቅዋል።

ጀርመንዊንግስ የተባለው አውሮፕላኑ ሉፍትሃንዛ አየር መንገድ እንዲህ አሰቃቂ አደጋ ሲያጋጥመው የትናትናው ከ40 ዓመታት በኃላ መሆኑ ተመልክተዋል።

አደጋው እሳዛኝ እና አሳስቢ መሆኑ በብዙ ሰዎች ላይ ያደረሰው ከፍተኛ ሐዘን ነው ሲሉ የሀገሪቱ መንግስት ቻንስለር ኤንጌላ መርክል መግለጣቸው ከበርሊን ከተማ የደረሰ ዜና አመልክተዋል።በዚህ ዓይነት ሁኔታ የሚያስፈልገውን ርዳታ እና ድጋ እንድያገኙ መንግስት የንሚቻለው ሁሉ ያድረጋል በማለት አክለው መግለጣቸው ዜናው አስታውቀዋል።

ከመንገደኞቹ መካከል 67 ጀርመናውያን ከነዚህ መካከል 16 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቦአት ተማሪዎች እና ሁለት መህራን እንደሚገኙባቸው ተገልጠዋል። የዚሁ አስቃቂ አደጋ መንስኤ በውል እንደምያታወቅ እና በመጠናት ላይ እንደሆነ እንዲሁም የአውሮፕላኑ የመረጃ መሰብሰብያ ሳጥን መገኘቱ እና የአደጋው መንስኤ ለማወቅ ሁነኛ ሚና እንዲጫወት ይጠበቃል።








All the contents on this site are copyrighted ©.