2015-03-25 14:26:00

አባ ሳሚር፦ በጸረ ታጣቂው እስላማዊ መንግሥት ትግል ሙስሊም አገሮች ግንባር ቀደም መሆን ይጠበቅባቸዋል


በየመን የሁቱ አማጽያን ኃይሎች የአገሪቱ ርእሰ ከተማ ሰንዓ በመቆጣጠር በአገሪቱ ደቡባዊና ምስራቃዊ ክልል መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት በማቀጣጠል መላ አገሪቱን ለመቆጣጠር ግስጋሴው እያፋጠኑ መሆናቸው ሲነገር፣ ከሥልጣናቸው የተነሱት በአደን የሚገኙት የአገሪቱ  ርእሰ ብሔር ሃይዲ በዚህ በተከስተው ግጭት የኢራን ጣልቃ ገብነት አለበት ሲሉ፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ከጋልፍ አገሮች የትብብር ማኅበር ድጋፍ መጠየቃቸው የጠቆሙት ከአገሪቱ የሚሰራጩ ዜናዎች አክለውም፣ በአገሪቱ ሥልጣን ለመጨበጥ በተደጋጋሚ የሚታይ የእርስ በእርሱ ግጭት ለአልቃይዳ አሸባሪያን ኃይሎች ብሎም ገዛ እራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ ለሰየመው በመካከለኛው ምስራቅና በሰሜን አፍሪቃ ክልል የሽበራ ጥቃቱን እያስፋፋ ላለው ፅንፈኛው ታጣቂው ኃይል አመች ሁኔታ መሆኑ ያመለክታሉ።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም በበይሩት ቅዱስ ዮሴፍ መንበረ ጥበብ የሥነ ዓረብ ባህልና ታሪክ እንዲሁ የሥነ ምስልምና ባህል መምህር የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ሳሚር ክሃሊል ሳሚር በመካከለኛው ምስራቅና በስሜን አፍሪቃ በጠቅላላ የምስልምና ሃይማኖት ብዙሃን በሆነባቸው አገሮች እየገሰገሰ ያለው እስላማዊ መንግሥት በማለት ገዛ እራሱ የሰየመው ፅንፈኛው ታጣቂው ኃይል ከሶሪያና ከኢራቅ ማዶ በተለያዩ አገሮች ውጥረት እየጫረ፣ ወደ ሊቢያ ከዚህ በመቀጠልም በየመን የእርስ በእርስ ግጭት እንዲፋፋን እያደረገ ነው። በቱኒዝ የተከሰተው ጥቃት ምስክር ነው።

በሁሉም አገሮች ውስጥ እንገኛለን ኃያላን ነን ምንም ነገር አንፈራም በሁሉም አገሮች ስውር አባላት አሉን የሚል መልእክት እያስተጋቡ ናቸው፣ እርግጥ ነው የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ይኸንን እስላማዊ መንግሥት እያስፋፋው ላለው ግብረ ሽበራ ለመግታት ብሎ ካለመ ብዙ ዓረብ አገሮች መቆጣጠር ይኖርበታል ማለት ነው። ስለዚህ ሁኔታው ከዚህ አንጻር ሲታይ  የሚቻልም አይደለም። የአጥፍተህ ጥፋ ጥቃት ለመቆጣጠር ያዳግታል፣  ፅንፈኛው ታጣዊ ኃይል በሚቆጣጠርው ክልል ነዋሪ ሕዝብ ጋር ተቀላቅሎ የሚኖር በመሆኑ ለይቶ በአየር ኃይል በተሸኘ ጥቃት ለመምታትም አይቻልም። በመሆኑም መፍትሔው በምድር ጦር የተሸኝ ጥቃት ከዚህ ጋር በማያያዝም ጸረ እስላማዊ መንግሥት ለሚታገሉት በተለያዩ አገሮች ለሚገኙት የመከላከያ ኃይልና ለጸረ እስላማዊ መንግሥት ኅብረሰብ በቂ ድጋፍ ማቅረብ፣ በጦር መሣሪያ ኃይል መደገፍ ያስፈልጋል። ሆኖም የሚሰጠው የጦር መሣሪያ ድጋፍ በእስላማዊ መንግሥት ታጣቂው ኃይል እጅ እንዳይገባ ጽኑ ክትትል ወሳኝ ነው። እስላማዊ መንግሥት ለማጥፋት በሚደረገው ትግል እስላም አገሮች ግንባር ቀደም ተሳታፊነት አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው። በእስላም አገሮች መሠረታዊ ለውጥ ለመጨበጥ የባህል አብዮት የሃይማኖት አብዮት ማረጋገጥ ያስፈልጋል፣ መፍትሔው በእስላም አገሮች ከእስላም አገሮች ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።        








All the contents on this site are copyrighted ©.