2015-03-24 12:40:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንሲስ በጽንፈኞች እየታመሰች ለምትገኝ ናይጀርያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት መልዕክት ላኩ


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በጽንፈኞች እየታመሰች ለምትገኝ ናይጀርያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት መልዕክት መላካቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቀዋል፣

በዚሁ የቅድስት መንበር መግለጫ መሰረት ቅድስነታቸው ለብጹዓን ጳጳሳት ናይጀርያ የላኩት መልዕክት በጽንፈኞች ዓመጽ የተነሳ በመሰቃየት ላይ ከሚገኙ ናይጀርያውያን ጐን መሆናቸው እና ሀገሪቱ ውስጥ ሰላም ይወርድ ዘንድ እየጸለዩ መሆናቸው በላኩት መልዕክት አስገንዝበዋል።

ብጹዓን ጳጳሳት ናይጀርያ ሀገሪቱ ውስጥ ሰላም እንዲመጣ የሰላም መንገድ በመከተል ሰላምን እንድያፈላልጉ የቅድስነታቸው መልዕክት አውስቶ በሀገሪቱ የክርስትያን እና እስላም ማሕበረ ሰቦች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ዓመጽ እንዳሳሰባቸው ማመልከቱ መግለጫው አክሎ ገልጠዋል።

በህዝብ ብዛት ከአፍርቃ ሀገራት የላቀች የናይጀርያ ሕብረተ ሰብ ፍትሐዊ እና በትብብር ላይ የተመረኮሰ እንዲሆን የናይጀርያ ብጹዓን ካቶሊካውያን ጳጳሳት የመሪነት ሚና እንዲጨወቱ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የላኩት መልእክት ማሳሰቡም ተመልክተዋል።

በቅድስት መንበር የተሰጠ መግለጫ እንዳስገነዘበው ፡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ  ለናይጀርያ ብጹዓን ጳጳሳት የላኩት መልዕክት በጳጳሳቱ በኩል  ለሀገሪቱ መነኵስያት መነኮሳን ካህናት ደናግላን ለትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች  ለሚስያናውያን ማለት ልዑካነ ቅዱስ ወንጌል እና ለምእመናን  እንዲደረስ ጠይቀዋል።

ባለፉት ዓመታት ቦኮ ሐራም የተባለ ጽንፈኛ ቡድን በርካታ ክርስትያኖችም ሆነ እስላሞች  በግፍ መግደሉ ማቁሰሉ እንዲፈናቀሉ ማድረጉ መጥለፉ  በህዝብ ላይ ዓመጽ መፈጸሙ  የሚያሳዝን ክስተት መሆኑ መልዕክቱ ጠቁሞ ይህ  በፍጥነት መገታት ያለበት ጉዳይ እንደሆነ አመልክተዋል።

በሃይማኖት ስም የሚጸም ዓመጽ ሁሉ እኩት ተግባር መሆኑ እና ሃይማኖቱ የሚያራክስ ተግባር ከመሆኑ ባሻገር ለራስ ጥቅም የሚፈጸም ተግባር እንደሆነ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለናይጀርያ የላኩት መልዕክት ማስታወቁ ተያይዞ ተገልጠዋል።

ለግዙፍ አፍሪቃዊት ናይጀርያ የገጠማትን ፈተና ትልቅ መሆኑ እና እሳቸው በጸሎት እና በመንፈስ ከሀገሪቱ  ህዝብ አጠገብ  መሆናቸው ጠቅሰው ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐውርያቱ  ሰላም እተውላችሁለሁ ሰላሜን እሰጣችሁሀለሁ እንዳላቸው ሰላም የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ሰላም እና የሰላም ንጉስ  እነደሆነ  ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለናይጀርያ ጳጳሳት የላኩት መልዕክት  ማስገንዘቡ በቅድስት መንበር የተሸጠ መግለጫ  አስታውቀዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ የናይጀርያ ኒጀር ቻድ እና ካመሩን መንግስታት ቦኢካ ሐራም የተባለውን እስላማዊ ጽንፈኛ ቡድኑ ጥቃት ለመግታት አጋርነት መፍጠራቸው የሚታወስ ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.