2015-03-23 15:13:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በፖጆረአለ ወኃኒ ቤት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚህ እ.ኤ.አ. መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. በናፖሊ ከተማ ባካሄዱት ሐውፆተ ኖልዎ፣ በከተማይቱ በሚገኘው ፖጆረአለ ወኃኒ ቤት በመሄድ እዛው ከሚገኙት እስረኞች ጋር ተገናኝተው መሪ ቃል ለግሰው አብረው ምሳ መቋደሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ ሳባቲነሊ አስታወቁ።

“ከእግዚአብሔር ፍቅር የሚለየን ምንም ነገር የለም፣ የወኅኒ ቤቶች አጥር በሮች ከዚህ ፍቅር አይለዩንም፣ እግዚአብሔር ከእኛ የሚጠብቀው በኃጢአታችንን ተጸጽተን ምስጢረ ንስሃ ተቀብለን ወደ እርሱ መመለስን ነው። ኃጢአታችን ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት ሥፍራ መሆን አለበት፣ ከእርሱ ምኅረት ጋር የምንገናኝበት የንስኃና የጸጸት ሥፍራ መሆን አለበት” ያሉት ቅዱስ አባታችን፣ ይኸንን ለእስረኞች ያስደመጡት ሁሉንም በተለያየ ምክንያት ተለይቶ በብቸኝነት ሕይወት የሚኖር በከተሞቻችን ጥጋ ጥግ ለገዛ እራሱ ተትዎ የሚኖረውን ሁሉ የሚመለከት ሲሆን የእስረኞች ሁኔታ ዕለት በዕለት ከተለያዩ ወኃኒ ቤት ከሚገኙት እስረኞች በሚደርሳቸው ደብዳቤ ብቻ ሳይሆን ካህን ከዛም የቦኖስ አይረስ ሊቀ ጳጳሳት እያሉ በወህኒ ቤቶች ይፈጽሙት ከነበረው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ገጠመኝ ምክንያት ጠንቅቀው የሚያውቁት ጉዳይ መሆኑ ያስታወሱት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሳባቲነሊ አያይዘው በተለያየ የተልእኮ ዘርፍ በወህኒ ቤት አገልግሎት የሚሰጡት ሁሉ ለእስረኞች ቅርብ በመሆን፣ እያንዳንዱ እስረኛ የተበየነበት እስር አመታት አጠናቆ ከኅብረተሰብ ጋር በሰላም ተቀላቅሎ ለመኖር የሚያበቃው ሕንጸት በማቅረብ ከተሞቻችን የፍትና የሰላም ሥፍራ እንዲሆኑ በማድረግ ተልእኮ የተጠሩ መሆናቸው ቅዱስ አባታችን አብራርተው፣ ወኅኒ ቤቶች የቅጣት ሥፍራ ሳይሆን የለውጥና የኃዳሴ ሥፍራ መሆን አለባቸው እንዳሉ ሳባቲነሊ አስታወቁ።

“ብዙውን ጊዜ የተረሳን በሁሉም የተተውን፣ ሆነን ሊሰማን ይችላል፣ ሆኖም ግን እግዚአብሔር ፈጽሞ አይረሳንም፣ እግዚአብሔር ልጆቹን ፈጽሞ አይረሳም፣ ከጎናችን ነው። በተለይ ደግሞ በከባድ ፈተና ስንገኝ በበለጠ ቅርባችን ይሆናል። ይኽ እምነት በከባድ ስቃይና ችግር ስንገኝ መጽናናትና ተስፋችን ይሆናል። ጌታ እኛን ከመጠባበቅ አይሰለችም፣ ከእርሱ ጋር እንገናኝ ዘንድ በመጠባበብቃችን አይደክምም፣ መጻኢ በእግዚአብሔር እጅ ነው የሚል እማኔ የክርስቲያን እውነተኛ ተስፋ ነው” በማለት ያስደመጡት ምዕዳን እንዳጠቃለሉ ሳባቲነሊ አስታወቁ።           








All the contents on this site are copyrighted ©.