2015-03-20 18:44:00

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፤


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ!

ባለፉት ትምህርቶቻችን የቤተ ሰብ ሕይወት በሚመለከት ቤተሰብን ስለሚያቆሙ እናት አባት ልጆች ወንድሞች እኅቶችና አያቶች ከተመለከትን በኋላ ዛሬ ስለሕጻናት በመናገር ላገባድደው እወዳለሁ፣ ይህንን ደግሞ በሁለት ምዕራፎች እንመለከተዋለን፣ በዛሬው ዕለት ሕጻናት ለሰው ልጅ ምንኛ ያህል ትልቅ ስጦታ መሆናቸውን እንመለከታለን፣ እውነት ነው ታላቅ ስጦታ ናቸው ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ሊወለዱም ስለማይፈቅዱላቸው እጅግ የተገለሉም ናቸው፤ ይህንን በሚመለከት አንዳንድ ሕጻናትን እጅግ የሚጐዱ ቍስሎች እንመለከታለን፣ በኤስያ ባደረግሁት ሓዋርያዊ ጉብኝት ያገኝህዋቸውን ሕጻናት ሳስተውስ ሕይወት የሞላቸውና ደስተኞች መሆናቸውን ሳሰላስል በሌላ በኩል ደግሞ በዓለማችን ከፍቶዋቸው የሚኖሩ ሕጻናትን አስባለሁ፣ እንደ እውነቱ ከሆነ አንድን ማሕበረ ሰብ ከሕጻናቱ አያያዝና የሕይወት ኑሮ መገመት ይቻላል፣ ይህም በሞራላዊ አመለካከት ብቻ ሳይሆን በኅብረተሰባዊ አካሄድም ሲያስገምት ማሕበረ ሰቡ ነጻነት ያለው ወይንም  የአለም አቀፍ ጥቅምን ብቻ የሚመለከት የእርሱ ባርያ መሆኑንም ያስገነዝባል፣

ሕጻናትን ስንመለከት በመጀመሪያዎቹ የሕይወት ዓመታት ሁላችን ሙሉ በሙሉ በሌሎች ሰዎች እንክብካቤና ፍቅር ጥገኞች መሆናንችን ያስታውሰናል፣ የእግዚብሔር ልጅም ከዚህ ሁኔታ አላመለጠም፣ ይህም በየዓመቱ የልደት በዓል ስናከብር የምንሰላስለው ምሥጥር ነው፣ የልደት በዓል ላይ የምናዘጋጀው የኢየሱስ ሕጻን ግርግም ይህንን ምሥጢር በቀጥታና በቀላሉ የሚገለጽልን ምልክት ነው፣

ሌላው በጣም የሚገርመው ነገር ደግሞ፡ እግዚአብሔር በሕጻናት እንዲታወቅና እንዲረዳ እንደማያስቸግረው ሲሆን እንዲሁም ሕጻናትም  እንዲረዱት አይቸግራቸውም፣ ኢየሱስ ሕጻናትን አስመልክቶ በመጽሐፍ ቅዱስ ደስ የሚሰኙና ጠንካራ ቃላቶች የሚናገረውም የአጋጣሚ ነገር አይደለም፣ ሕጻናትና ትንንሾች የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሌሎች እንክብካቤና እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ሲያመለክት በተለይ ሕጻናትን ነው፣ ለምሳሌ ብንወስድ ኢየሱስ “የሰማይና የምድር ጌታ የሆንህ አባት ሆይ! ይህን ነገር ከጥበበኞችና ከአዋቂዎች ሰውረህ ለሕፃናት ስለገለጥክላቸው አመሰግንሃለሁ”(ማቴ 11፤25) ይላል፣

እንዲሁም “ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱንም እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፡ በሰማይ ያሉት የእነርሱ መላእክት በሰማይ ባለው በአባቴ ፊት ሁልግዜ ይገኛሉ።”(ማቴ 10፤18) ይላል፣

ስለዚህ ሕጻናት ለሕብረተሰቡና ለቤተክርስትያን ሃብት ናቸው፣ ምክንያቱም ወደ እግዚብሔር መንግስት መግባት የሚያስፈልገው ቅድመ ሁኔታ እንደ ሕፃናት መሆን እንዳለብን ወንጌል በተደጋጋሚ ሳያቋርጥ ያሳስበናል፣ ይህም በገዛራሳችን ተማምነን በቃኝ ለማለት ሳይሆን የግድ እርዳታ ፍቅርና ምሕረት እንደሚያስፈልገን ለማስረዳት ነው፣ ሁላችንም እርዳታ ፍቅር እና ምሕረት ያስፈልገናል፣

ሌላው ሕፃናት የሚያሳስቡን መልካም ነገር ደግሞ እኛ ሁላችን ልጆች መሆናችንን ነው፣ በእርግጥ ምንም እንኳን ብናድግ ወይንም ብንሸመግል እንዲሁም ወላጆች ብንሆን የኃላፊነትን ቦታ ብንይዝም ሁሌ መታወቂያችን ልጆች መሆናችንን አይዘነጋም፣ ሁላችንም የሰማያዊ አባት ልጆች ነን፣ ይህም የሚገልጥልን ሕይወት በስጦታ የተቀበልናት እንጂ በራሳችን ፈቃድ እንዳልተፈጠርን ነው፣ ስለዚህ ሕይወት  ከእግዚአብሔር የተቀበልነው ታላቁ የመጀመሪያው ስጦታ ነው፣ አንዳንዴ ይህንን እንዘነጋለን፤ ልክ እኛ የሕይወታችን ጌቶች እንደሆንን እንኖራለን፤ ነገር ግን እንዲህ አይደለም ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሔር ጥገኞች ነን፣

በእውነቱ በጣም የሚያስደስተውና የሚገርመው የሕይወት ኑራችን በማንኛውም ደረጃና ሁኔታ ቢገኝም ልጅነታችንን ማንም አይቀማውም፤ ሁሌ ልጆች ነን፣ ከሕጻናት የምንማረው፡ የመጀመሪያው መልእክት ይህንን ነው፣ ሕፃናት በአጠገባችን ሲገኙ ብቻ ነው ሁላችንም ልጆች እንደሆንን የምናስታውሰውና የምናውቀው፣

ሕፃናት ለሰው ልጅ የሚሰጡት ሃብትና ስጦታ ብዙ ነው፣ በጥቂቱ ላስታውሳችሁ፤ ሕጻናት በተጨባጭ መልካም ነገር ባይኖር እንኳን የወደፊቱን በግልጽነትና በንጹህ ዓይን በመመልከት መልካም እንደሆነ ያምናሉ፣ ልጅ እናትና አባቱን ሳይጠራጠር ሙሉ ለሙሉ እንደሚተማመን እንዲሁም በአምላኩ በኢየሱስና በእመቤታችን ድንግል ማርያም ይተማመናል፣ በዛውም ልክ ልቡ  ጥርጥር ክፋትና ደንዳናነት ያልተሞላ ንጹሕና ያልተበከለ ልብ ነው ያለው፣ ይሁን እንጂ ሕፃናት ቢሆኑም የአዳም ኀጢአት አለባቸው፣ ምንም እንኳ ስግግብነት ቢያጠቃቸው ልባቸው ንጹሕና ቅኑ ነው፣

ሕጻናት አስመሳዮች አይደሉም፤ የሚሰማቸውን ያዩትን በግልጽና በቀጥታ ይናገራሉ፣ ብዙውን ግዜ ሰዎች ፊት የመሰላቸውን ስለሚናገሩ ወላጆችን ችግር ውስጥ ይከታሉ፣ ለምሳሌ በሰው ፊት የማያስኬድ ነገር ሲያዝዋቸው፤ እንቢ! ይህ አስቀያሚ ነው! በማለት ግልጽ በሆነ መንገድ ይናገራሉ፤ ይህም የሚሆንበት ምክንያትም ገና የአዋቂዎች አስመሳይነት ስላልታማሩ ነው! እኛ አዋቂዎች አስመሳዮች ነን፣

እንዲሁም ሕጻናት በተፈጥሮ ስጦታቸው ፍቅርና ርሕራሄን ከሌሎች መቀበልና ለሌሎችም መለገስ ይችላሉ፣ ርህራሄ ማለት የደነደነ ልብ እንደ አለት ሳይሆን ግን ልባችን እንደ ለሰለሰ ሥጋ ማለት ነው፣ በትንቢተ ሕዝቅኤል እንደተጻፈው አዲስ ልብንም እሰጣችኋለሁ፡አዲስ መንፈስንም በውስጣችሁ አኖራለሁ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ” (36፡26) ይላል፣ እዚህ ላይ መገንዘብ ያለብን የልብ መለስለስ ወይንም ርህራሄ ሲል ልዩ ጣዕምና ትርጉም ያለው ቅኔያዊ አነጋገር ነው፣ ስለዚህ ሁኔታዎችንና የተከሰቱት ነገሮችን እንደ ማንኛው ነገር አድርጎ ለግዝያዊ ጥቅም ብቻ መመልከት የለብንም፣

ሕፃናት ማልቀስና መሳቅን ይችላሉ፣ አንዳንድ ሕፃናት ሲያቅፋቸው ይስቃሉ አንዳንዱ ነጭ ልብስ ለብሼ ሲያዩ ሃኪማቸውን ክትባት ሊከተቡ ያዩ ይመስላቸዋል መሰለኝ ያለቅሳሉ ልጆች በቀላሉ የሚስቁና የሚያለቅሱ ሲሆኑ አዋቂዎች ግን ለዚህ ሳቅና ለቅሶ በቀላሉ የታገዱ ይመስላሉ ብዙ ግዜ እኛ አዋቂዎች የእውነት ሳቅ የለንም የውሸት ፈገግታ ነው ያለን፣ ሳቅም ለቅሶም የሚመነጨው ከልብ ነው፣ አብዛኛውን ግዜ ልባችን ምንድነው የሚያግደው በቀላሉ እንዳንስቅና እንዳናለቅስ? እኛ አዋቂዎች ከሕፃናት እንማር እራሳችንን እንጠይቅ ውስጣችንን እንመልከት፣

ለዚህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛምርቱን  እንደ ሕፃናት እንዲሆኑ የሚሳስባቸውና የሚጋብዛቸውን ምክንያት ሲገልጥ፤ “በእውነት እላችኋለሁ ካልተለወጣችሁና እንደ ሕፃናት ካልሆናችሁ ወደ መንግሥተ ሰማይ ከቶ አትገቡም። እየሱስም ይሕን በማየት ተቆጥቶ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው የእግዚብሔር መንግስት እንደዚህ ላሉት ስለ ሆነች ሕጻናት ወደ እኔ ይምጡ ተው አትከልክላቸው” (ማቴ 18፡3 ማር 10፡14) ይላል፣

ውዶቼ! ሕጻናት በኑሮአችን ሕይወት ደስታና ተስፋ ያመጡልናል እንዲሁም ችግርም ያመጡብባል! ምን ይደረግ ሕይወት እንደዛ ነውና፣ እርግጥ ነው ብዙ ችግርና ውጣ ውረድ ያስከትላሉ ነገር ግን ሕጻናት ከሌለው ማኅበረሰብ በእነዚህ ሁኔታዎች የተቸገረ ማኅበረሰብ ይመረጣል ምክንያቱም ሕይጻናት የሌለበት ማኅበረሰብ ኃዘንተኛ ብቸኛ ነውና፣ በአንድ ማኅበረሰብ የወሊድ ደረጃ እስከ አንድ ከመቶ የወረደ እንደሆነ ይህ ማኅበር ኃዘንተኛ ነው ሕጻናት የሉትምና፤ ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.