2015-03-20 19:09:00

በፍቅር የሚያገልግል ብቻ እውነተኛ ጠባቂ ሊሆን ይችላል።


የቅድስት ቤተሰብ ጠባቂ የሆነ የቅዱስ ዮሴፍ ክብረ በዓል በላቲኑ ሥርዓት ትናንትና ተዘክሮ ዋለ፣ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በአለም አቀፋዊ የእረኝነት ተልእኮዋቸው እንደ መሪና ጠባቂ የቅዱስ ዮሴፍን አርአያነት መከተልን እንደሚወዱ ሲገለጥ ይሕም “ቅዱስ ዮሴፍ የመለኮታዊ ጥበብ ምሳሌ መሆኑን በመጥቀስ ነገሮች ሳይረዱትና ግራ ሲገባው ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔርን እንደጠየቀና እንዲሁም በናዝሬት ቤታቸው ለኢየሱስና ለእናቱ እንዳገለገላቸው ነው” በማለት ይገልጡታል፣

በማያያዝም የቅዱስ ዩሴፍን መልካምነት ሲገልጹ፤ “ማን ነው ለትዳር እየተዘጋጀ ፍቅረኛው ከትዳር በፊት ከሱ ያልሆነ ብትጸንስ እሺ የሚለው! ማንስ ወንድ ነው በእንዲህ አይነት የሕይወት ፈተና ፊት ክብሩን ለማስከበር ንዴቱን ወይንም እልኩን የማይወጣው!ዘመናዊ ተብለው የሚታዩ ፊልሞች እንኳን እንዲህ አይነቱን የሕይወት ፈተና ሊያቀርቡም ሊያሳዩም አልሞከሩም። ምክንያቱም የወንዶችን ባሕሪ በፊልም ሲተላለፍ በዘመናት የምንመለከተው ነጭናጮች በራሳቸው የማይተማመኑ በተለይም በአባትነት በባልነት ደረጃ የመረዳትና የሃላፊነት አቅሙ የሌላቸውና ጭራሽ ባሁን ወቅት አባትና ባል የሚለውን ቃል ቢሰረዝ ወይንም ባይኖር ይመርጣሉ፣ ቅዱስ ዮሴፍ ግን ምንግዜም የእግዚብሔርን ድምፅ የሚሰማ ሰው ከመሆኑም ባሻገር በጥንቃቄ ልቡን የሚያዳምጥና ለሚመጣለትም የአምላኩን መልእክት በጥሞናና በጥንቃቄ ይቀበል ነበር። በሕይወት ዘመኑ የራሱን ምርጫና ምኞት አልፈጸመም። እራሱን ለማስደሰት በደረሰበት የሕይወት ፈተናም ቂምና እልሁን አልተወጣም። ግን በጣም በሚያስገርም ሁኔታ የመጣለትን የአምላኩን ትዕዛዝ ለመታዘዝ መዘጋጀቱን እንማራለን፣ ቅዱስ ዮሴፍ የሚመራሙ ሁሌ በአምላኩ ነበር የዛሬ 2 ሺ አመት በፊት የሰው ልጅ ፍቅር በሚደንቅና በሚገርም መቀየርና መገለጽ እንደሚቻል ያስተማረን ቅዱስ ዮሴፍ ነው። የሰው ልጅ በራሱ ከመዘጋት ይልቅ ወደ አምላኩ ቢመለከትና ለአምላኩ ቢከፈት ትልቅ ነገር ነው። ቅዱስ ዮሴፍ ከሰማይ እርዳታ በፊት በራሱ ከልቡ ለሚያፈቅራት ሴት ርህራሄና መረዳት ኖረው። ሌሎች በሱ ቦታ ቢሆኑ ንቀት ውርደትና መፍትሄ ባልኖረ ነበር። እሱ ግን እጮኛውንና በማሕጸን ውስጥ የነበረውን ልጇን ሊወድና ሊያገለግል እራሱን አቀረበ። ከነሱም ጋር አብሮ ለወደፊት ለሚያጋጥማቸው የሕይወት ፈተናዎች አብሮ እንደተፈተነም ነው፣ ቅዱስ ዮሴፍ አደራ ጠባቂ ነው፤ ምክንያቱም  አምላኩን ማዳመጥ በመቻሉና በራሱ ፈቃደኝነትና ምኞች ባለመመራቱ ነው። በጥንቃቄ አደራ የተሰጡትን ሰዎች እንደጠበቀና ለወደፊትም  የሚመጣውንና የሚያጋጥሙትን  ሁሉ አስቀድሞ የመረዳት ችሎታ እንደነበረውም፤ ከአካባቢውም ይጠነቀቅና ውሳኔዎችንም በብልህነት መወሰን ይችል እንደነበር ነው፣ ውዶቼ ከቅዱስ ዮሴፍ ለክርስቶስ ጥሪ እንዴት መልስ መስጠት እንዳለብን እንማራለን። እራሳችንን ለእግዚብሔር በማቅረብና በማዘጋጀት። እንዲሁም የክርስቲያኖች ጥሪ ማእከል ክርስቶስ መሆኑን እንመለከታለን። ስለዚህ ክርስቶስን በልባችንን እናኑሮም ሌሎችንም በልባችን ማስታወስ እንድንችል ተፈጥሮንም በእንክብካቤ እንጠብቅ፣ እግዚአብሔር ለቅዱስ ዮሴፍ በሕልሙ ሲገለጥለት ማድረግ ያለበትን ይነግረው ነበር ባይረዳውም እሺ ብሎ ይታዘዝ ነበር። ስለዚህ ለእግዚብሔር አስቀድሞ የሚታዘዝ ሰው ማንኛውንም ሰው ለማቀፍ እጆቹ የተዘረጉ መሆናቸውን በማስተማር ቤተክርስቲያንም እንዲሁ ለወደቁትና ለደከሙት ወገኖችዋ እንደ ቅዱስ ዮሴፍ በፍቅር ለመርዳትና ለማገልገል አደራ አላት” ሲሉ አስገንዝበዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.