መታወቂያ ገጽየቫቲካን ሬድዮ
የቫቲካን ሬድዮ   
more languages  
የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ (እ.ኤ.አ. የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም.)
ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ዓቢይ ጾም ፊት ለፊት ጸረ የክፋት መንፈስ የምንታገልበት ወቅት ነው


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ “ዓቢይ ጾም ጸረ የዲያብሎስ ወጥመድ የምታገልበትና ከዚህ ጥብቅ ትግል የልብ መለወጥ የሚፈልቅበት ወቅት ነው” በሚል ቅዉም ሓሳብ ላይ ያነጣጠረ አስተንትኖ እ.ኤ.አ. የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም. እኩለ ቀን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ሁሌ እንደተለመደው በላቲን ሥርዓት የዕለተ ሰንበት ምንባብ ተንተርሰው የሚለግሱት ስብከት እንዳቀረቡ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አክለው፣ ቅዱስ አባታችን የለገሱት ስብከት አጠቃለው ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር አሳርገው እንዳበቁም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከውስጥና ከውጭ ለተሰበሰበው ምእመን ሁሉ በዚህ የዓቢይ ጾም ወቅት ለግል አስተንትኖ የሚደግፍ አንድ አነስ ያለ የአቢይ ጾም የአስተንትኖ መጽሓፍ መለገሳቸው አስታውቀዋል።
ከክፋት መንፈስ ጋር እጅ ልእጅ የምንገጥምበት የምንታገልበት ሁነት የጸጥታና የዲያብሎስ ወጥመድ ለይተን የምናውቅበትና በእግዚአብሔር እርዳታ ድል የምንነሣበት ጊዜና ቦታ እንደሚያስፈልግ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በለገሱት ስብከት አብራርተው፣ ልክ ጌታችን ኢየሱስ በአሕዛብ ዘንድ ተልእኮው አንድ ብሎ ከመጀመሩ በፊት ገዛ እራሱን ሰብሰብ ለማድረግ በሱባኤ መልክ ምድረ በዳ እንደ መረጠ አስታውሰው ይኸንን መሠረት በማድረግ ከነፍሳችን ውጭና ውስጥ ምድረ በዳ ያለው አስፍፈላጊነት ገልጠው “ኢየሱስ በዚያ  ...»ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም ሶበ ይሄልው አኀው ኅቡረ (መዝ 132፤1)!

RealAudioMP3 የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ!
ውድ ወንድሞችና እኅቶች! ሰላም እንደምን አደራችሁ! ስለቤተሰብ በምናደርገው ትምህርተ ክርስቶስ አባት እናትና ልጆች በቤተሰብ ያላቸውን ሚና ተመልክተን ነበር፣ ዛሬ ደግሞ ስለወንድማማችነት ማለትም ስለ እህትና ወንድም የሚለውን እንመለከታለን፣ እነዚህ ቃላት ክርስቲያኖች በጣም የሚያፈቅሯቸው ቃላት ናቸው፣ ለዚሁ ዓይነት የቤተሰብ መተሳሰር ምስጋና ይግባው፤ እነኚህ ቃላት በተለያዩ ባሕሎችና የታሪክ ዘመናት ሁሉም የሚረዳቸው ቋንቋ ሆነዋል፣
የወንድሟሟችነት መተሳሰር በእግዚአብሔር ሕዝብ ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ አለው፤ እግዚአብሔር ለሕዝቡ የተገለጠውም በሰው ልጅ ሕይወት  ...»በጽንፈኞች በዓመጽ የተገደሉትን የግብጽ ክርስትያን
እ/ር እንደ ሰማዕታት ይቀበላቸው ር.ሊ.ጳ. ፍራንሲስ ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቅድስት ማርታ ቤተ ጸሎት መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ግዜ ኢሲስ በተባለ ጽንፈኛ እስላማዊ ቡድን ሊብያ ላይ ሀያ አንድ የግብጽ ክርስትያኖች በአሰቃቂ መንገድ እንደገደላቸው በማስታወስ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጠው ከሃሌ ኩሉ እግዚአብሔር በመንግስተ ሰማያቱ እንደ ሰማዕታት እንዲቀበላቸው ጸልየዋል። በማያያዝም ለቤተ ሰቦቻቸው ጥናቱ እንደሰጠታቸው እንደሚጸልዩ አገንዝበዋል ቅድስነታቸው እግዚአብሔር የዓመጸኞች ልቦች እንዲቀይር በመካከለኛው ምስራቅ ሰላሙ እንድያወርድም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሰማይ እና ምድር የፈተጠረ እግዚአብሔርን እንልመን ብለዋል።ቅዱስ አባታችን ርእሰ  ...»


የካርዲናል ሥራ “ከቤተ ክርስትያን የራቁትን አለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈልግና ማንንም አለማግለል” ነው፣

RealAudioMP3 ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቅዳሜ ዕለት የካርዲናልነት ሥልጣን ከሰጥዋቸው 20 አዳዲስ ካርዲናሎች ጋር የምስጋና መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉት ጊዜ የአዳዲስ ካርዲናሎች ዋና ሥራ “ከቤተ ክርስትያን የራቁትን አለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈልግና ማንንም አለማግለል” እንደሆነ ገልጠዋል፣
የቤተ ክርስትያን መንገድ አለምንም ቅድመ ሁኔታና ፍራቻ ከእርሷ የራዉት መፈለግ ሲሆን አዳዲስ ካርዲናሎቹም ጌታ ኢየሱስ በዘመኑ በፍራቻና በቅድመ ሁኔታ በገዛ ራሳቸው ተዘግተው ለነበሩ እንዳናወጠ ሁሉ ፈሩን በመከተል በዘመናችን በተለያዩ ምክንያቶች ተገለው ለሚገኙ ሰዎች ማገልገል እንዳለባቸውም አሳስበዋል፣ ምናልባት ይህ  ...»የካርዲናሎች ጉባኤና ምክርቤት በቫቲካን ከተማ ውስጥ፤

RealAudioMP3 በቫቲካን ከተማ የሲኖዶስ አዳራሽ ለሁለት ቀናት የተካሄደው የካርዲናላት ምክር ቤት ዛሬ መፈጸሙ ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል።
ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዚሁ ምክር ቤት ተሳታፊ በሆኑበት ግዜ እናዳመለከቱት የቅድስት መንበር የምህደራ በአዲስ መልክ ማዋቀር ተሐዶሶ ለክርስትና ምስክርነት ሁነኛ መሳርያ እንደሆነ ማስገንዘባቸው መግለጫው አክሎ አመልክተዋል።

ይህ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የተመሰረተ በዘጠኝ ካርዲናሎች የቆመ ምክር ቤት አዲስ ሐዋርያዊ ሕገ ቆኖና ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እንድያረቅ እንደሚጠበቅ የሚታወስ ነው ።
ይሁን እና የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ  ...»የ.ር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፣

RealAudioMP3 ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ!
ባለፉት ቀናት በቤተሰብ ውስጥ የእናትና የአባት ቦታን አስመልክተን አስተንትነናል ዛሬ ደግሞ ስለ ልጆች ለመናገር እወዳለሁ፣ ለትምህርቱ መግቢያ እንዲሆነን ከትንቢተ ኢሳያስ 60፡4-5 “ዓይኖችሽን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ፤ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ ይመጣሉ፥ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃ ላይ ይሸከሙአቸዋል።
በዚያን ጊዜ የባሕሩ በረከት ወደ አንቺ ስለሚመለስ፥ የአሕዛብም ብልጥግና ወደ አንቺ ስለሚመጣ፥ አይተሽ ደስ ይልሻል፥ ልብሽም ይደነቃል ይሰፋማል።” የሚለውን እንመለከታለን፣ ይህ ታላቅ የደስት ምልክት ሆኖ እውን የሚሆነውም ለብዙ ዘመናት  ...»ከዓለም 
የሮማዊት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ የመሥተዳድር መዋቅር ኅዳሴ

RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የቅርብ ተባባሪዎች ብፁዓን ካርዲናሎችና ብፁዓን ሊቀ ጳጳሳት በአቢይ ሐዋርያዊ ኃላፊነት አገልግሎት ሥር የሚያቅፈው መላይቱ ቤተ ክርስቲያን የሚመራው በኩሪያ ሮማና የሚጠራው የኩላዊት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ መሥተዳድር የበላይ መዋቅር ኅዳሴ ለማረጋገጥ የወጠኑት ዝክረ ነገር ዙሪያ የሚመክረው ዘጠኝ ብፁዓን ካርዲናሎች የሚያቅፍ በማድረግ ያቆሙት ምክር ቤት በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ ቅዱስ አባታችን በተገኙበት ስምንተኛው ጉባኤ እ.ኤ.አ. ከካቲት 9 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ እያካሄደ መሆኑ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ጉዳይ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና  ...»


ኡጋንዳ፦ ብፁዕ ኣቡነጁዘፐ ፍራንዘሊ፣ ሕፃናት ከውትድርናው ዓለም እናድን

እ.ኤ.አ. የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የጸረ ሕፃናት በውትድርናው ዓለም ቀን ታስቦ መዋሉ ሲገለጥ፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ሕፃናት ለተለያዩ ግጭቶች መገልገያ መሣሪያ እንዲሆኑ ታልሞ በውትድርናው ዓለም የማካተቱ ተግባር ከፍ እያለ መምጣቱ የሚያትቱ የተቀረጹት የጥናት ሰነዶች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መዋቅሮች መድረክ ለትርኢት ቀርቦ ሕፃናት ከዚህ አስከፊው ጸረ ሰብአዊ ተግባር ለማዳን የሚደረገው ርብርቦሽ እንዲያይል ጥሪ መተላለፉ የቫቲካ ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ዳቪደ ማጆረ ዕለቱን ምክንያት በማድረግ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
ገና ገዛ እራሳቸውን ለመከላከል ደረጃ ያልበቁት  ...»የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፦ አሰቃቂ ቅትለት በሴቶችና በሕፃናት ላይ

RealAudioMP3 ጀነቭ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብትና አስከባሪው ድርጅት ገዛ እራሱን እስላማዊ አገር ብሎ የሰየመው እስላማዊው አሸባሪው ኃይል በኢራቅ በሴቶችና በሕፃናት ላይ እንዲሁ በውሁዳን የአገሪቱ ዜቶች ላይ የሚፈጽመው ዘግናኝ አሰቃቂው ቅትለት በተመለከተ ባወጣዋ ልዩ ሰንድ ባሰፈረው ዘገባ ሕፃናት ለአጥፍተትህ ጥፋ የሸበራ ተግባር መገልገያ መሣሪያ በማድረግ ይኽ አልበቃ ብሎት የሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች ውሁዳን የኅብረተስብ ክፍል ቤተሰቦች በሕይወት እያሉ ቀብሮ ለሞት በመዳረግ በመስቀል ቸንክሮ አንገታቸውን በመቅላት ለሞት በመዳረግ ላቅመ አዳም የደረሱትና ያልደረሱት ውሁዳን የኅብረተሰብ አባላት ሴቶች በመድፈር ብሎም  ...»


የከፈኑ ሰው

RealAudioMP3 የቶሪኖ ከፈን በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ጥንታዊው በፍታ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተገነዘበት ጨርቅ ተብሎ የሚነገርለት በኢጣሊያ የቶሪኖ ሰበካ የሚገኘው ቅዱስ ከፈን እ.ኤ.አ. ቅዱስ ዮሐንስ ቦስኮ የተወለደበት ዝክረ 200ኛው ዓመት ምክንያት እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 19 ቀን እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ለትርኢት እንደሚቀርብ ከቶሪኖ ሰበካ የተሰራጨው መግለጫ ሲያመለክት፣ ባለፉት ቀናት ስለዚሁ ቅዱስ ከፈን በተመለከተ ኢየሱስ ናዝራዊ እንዲስተነተን ስቃዩ በጎልጎታ በጥልቅ ጽሞና የተኖረው ፍቅር ተጨባጭ መግለጫ በሚል ርእስ ሥር እንዲስተነተን የከፈኑ ተጨባጭ ሁነት ዙሪያ በካስተል ጋንዶልፎ ጳጳሳዊ ሕንጻ ቁምስና  ...»


በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የውሁድ ስምምነትና ውይይት ሳምንት

RealAudioMP3 ዘንድሮ አምስተኛው ዓለም አቀፍ የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የውሁድ ስምምነትና ውይይት ሳምንት እ.ኤ.አ. እስከ የካቲት 7 ቀን የሚዘልቀው መርሃ ግብር የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም. መጀመሩ ሲገለጥ፣ ይኽ እ.ኤ.አ. በ 2010 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ አማካኝነት የተነቃቃው የሁሉም ሃይማኖቶች የጋራው ግኑንነትና ውሁድ ስምምነት ሳምንት እ.ኤ.አ. በ2010 ዓ.ም. የዮርዳኖሱ ንጉስ አቡዱላህ ሁለተኛ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተገኝተው ባስደመጡት ንግግር “ሁሉም ሃይማኖቶች በሁሉም እንዲሰፍን አልመው የሚያስተምሩት ሰላም በሃይማኖት የእርስ በእርስ መቀባበልና እርስ በእርስ በመካባበር የሚገለጥ መሆን አለበት” በሚል  ...»RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ሐዋርያዊ ሕንጻ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አገረ ቫቲካን ለጉብኝት የገቡት የረፓብሊካዊት ከፕ ቨርድ መራሔ መንግሥት ኾሰ ማሪያ ፐረይራን ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።
ርእሰ ብሔር ኾሰ ማሪያ ፐረይራ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ተሰናብተው እንዳበቁም በሐዋርያዊ ሕንጻ በሚገኘው አቢያተ ፍርድ ተብሎ በሚጠራው የጉባኤ አዳራሽ በቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ተጠሪ በብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርት ከተሸኙት ከቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፅዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ጋር መገናኘቸው የጠቆመው ...»


ቤተ ክርስትያን በዓለም 
የ “Centesimus Annus-Pro Pontifice-መቶኛው ዓመት ደጋፊ ር.ሊ.ጳ. ማኅበር”

RealAudioMP3 በየሁለት ዓመት “Centesimus Annus-Pro Pontifice-መቶኛው ዓመት ደጋፊ ር.ሊ.ጳ. ማኅበር” ኤኮኖሚና ኅብረተሰብ ሰይሞ የቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ትምህርት ከኤኮኖሚና ቁጠባ ሂደት ጋር በማጣመር ለኤኮኖሚው ዓለምና ...»


ቅድስት መንበርና ኢራን

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. አገረ ቫቲካን የገቡትን የእስላማዊት ረፓብሊክ ኢራን ምክትል ርእሰ ብሔር ሓሂንዶክት ሞላቨርድን በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ በሚገኘው ሐዋርያዊ ቢሮአቸው ...»


ሢመተ አዲስ ቋሚ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሥር በሚተዳደሩት በምግብና እርሻ ድርጅት፣ በእርሻ ልማት ድርጅትና በዓለም አቀፍ የምግብ ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ሐዋርያዊ ልኡክ ሆነው እንዲያገለግሉ የቅድስት ...»


የወሲብ ዓመጽ ሰለባ ለሆኑት ዓለም አቀፍ የጸሎት ቀን

RealAudioMP3 የሕፃናትና ታዲጊ ወጣቶች ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ የሚከታተለው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መጋቢት ወር 2014 ዓ.ም. ያቆሙት ጳጳሳዊ ድርገት ምሉእ ጉባኤው በአገረ ቫቲካን ማካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፣ ስለ ...»


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ በቤተ ክርስቲያንና በኅብረተሰብ ለሴቶች ተጨማሪ ቦታ መስጠት

RealAudioMP3 ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ከየካቲት 4 ቀን እስከ የካቲት 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የሴቶች ሥነ ባህል፦ የሴቶች ባህል፣ በእኩልነትና በልዩነት (መሆናዊ መለያ)” በሚል ርእስ ሥር የተመራ ይፋዊ ...»አባ ጋብርኤለ ማርያ አለግራ የተባሉ ፍራንቸስካዊ መነኵሴና የቅዱስ መጽሓፍ ሊቅ ለመጀመርያ ጊዜ ቅዱስ መጽሓፍን በቻይና ቋንቋ የተረጐሙ ትናንትና ብፁዕ ተብለዋል፣ የብፅዕናቸው ሥነ ሥርዓትም በአቺረያለ ቤተ ክርስትያን አደባባይ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛን ወክለው እዛ በተገኙ የቅዱሳን ጉዳይ የምትከታተል ማኅበር ኃላፊ በሆኑ በብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ተፈጸመ፣ በሥርዓቱ የፓለርሞ ሊቀ ...»


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትናው ዕለት በሎረቶ ባደረጉት ሐዋርያዊ ዑደት እላይ እንደተጠቀሰው በቦታው ተገኝተው የተቀበልዋቸው ምእመናን ከ10 ሺ በላይ እንደሚሆኑ እንዲሁም መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ጊዜም በተለያዩ የሎረቶ አደባባዮችና ጐዳናዎች ከ50 ሺ ሕዝብ በላይ በመገናኛ ብዙሓን እንደተሳተፉ ከቦታው የመጣ ዜና አመልክተዋል፣ ከከተማው ከንቲባ ፓውሎ ኒኮለቲ ጀምሮ የመንግሥት ...»

የዕለተ ሰንበት ንባባትና ስብከት 

መዝሙር፡ ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ. . . . ። ንባባት፡ ፪ቆሮ 5፡16-ፍ፥1ጴጥ.1፡13-ፍ፥(ኢዩኤል 2፡12-18; ግ.ሓ.10፡17-30፥ማቴ 6፡16-23
ስብከት፡ “እግዚአብሔርሰ ሰማያት ገብረ፥ አሚን ወሰናይት ቅድሜሁ። ቅድሳት ወዕበየ ስብሓት ውስተ መቅደሱ” 96፡5።
የአባ ዳዊት ስብከትን ለማዳመጥ RealAudioMP3

 ...»


መዝሙር፡ ወብዙኃን ኖሎት መጽኡ ወስእኑ ከሢቶታ ለእብን. . . . . . . ።
ንባባት፡ ሮሜ 9፡1-17፥ 1ጴጥ 2፡20-ፍ፥ ግ.ሓ. 11፡1-9፥ ዮሐ 4፡1-27
ምስባክ፡
አግረረ ለነ አሕዛበ ወሕዝበ ታሕተ እገሪነ
ወኀረየነ ሎቱ ለርስቱ
ሥኖ ለያዕቆብ ዘአፍቀረ
የአባ ዳዊት ስብከት ለማዳመጥ RealAudioMP3

 ...»


መዝሙር፡ እሙነ ኮነ ልደቱ. . . . . . . ።
ንባባት፡ 2ቆሮ 1፡13-ፍ፥ 1ዮሓ 2፡22-ፍ፥ ግ.ሓ. 13፡20-27፥ ሉቃ 2፡42-ፍ።
የዕለቱ ምስማክንና ቃለ ወንጌል እንዲሁም የአባ ዳዊት ስብከት ለማዳመጥ RealAudioMP3
 ...»


RealAudioMP3 ዛሬ የምናነበው ወንጌል (ዮሐ 2፡1-14) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ ሠርግ ላይ ሰዎቹ ወይን ባለቀባቸው ጊዜ በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ውሃውን ወደ መልካም የወይን ጠጅ በመለወጥ ስላደረገው የመጀመሪያ ተዓምርና ራሱን ለዓለም እንደገለጠ እንዲሁም ሐዋርያቱ እንዴት በእርሱ እንዳመኑ ይናገራል፣፡ ይህ ወንጌል የሚያስተላልፍልንን ትምህርት በአጭሩ እንመለከተዋለን፣፡
በመጀመሪያ ...»


መዝሙር ይሠርቅ ኮከብ. . . . ።
ንባባት፡ ዕብ 11፡8-19፥ 1ዮሕ. 4፡1-9፥ ግ.ሓ. 7፡17-23፥ ማቴ 2፡1-12።
ስብከት ወአነሂ በኲርየ እረስዮ። ወልዑል ውእቱ እም ነገስተ ምድር፥ ውለዓለም አዓቅብ ሣህልየ። መዝ. 89፡፡27~28።
የአባ ዳዊት ስብከት ለማዳመጥ RealAudioMP3

 ...»


RealAudioMP3 የብፁዕ አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሱራፌል ደምረው
ሊቀ ጳጳስ ዘካቶሊካውያን ዘበኢትዮጵያ
የገና መልእክት፡

 ...»


መዝ፤ አቅዲሙ ነገረ በኦሪት
ንባብ፤ ሮሜ 13፡11-ፍጻሜ፤ 1ዮሓ 1፡1-ፍጻሜ፤ የሓዋ ሥራ 26፡12-19፤ ዮሐ 1፤1-19
ምስማክ፤ ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቀከ፤ እማንቱ ይምርሓኒ ወይሰዳኒ ደብረ መቅደስከ፤ ወውስተ አብያቲከ እግዚኦ፣
በዛሬው ሰንበት ከሚነበበው ወንጌል ኃይለ ቃል አድርገን የምንወስደው «ወደ ወገኖቹ መጣ፤ ወገኖቹ ግን አልተቀበሉትም ፤» የሚለውን ነው (ዮሐ፡ 1፡11)፡፡
RealAudioMP3
 ...»


መዝሙር፡ ዐርገ እምሃቤሆም አው ወረደ መንፈስ ቅዱስ. . . . . ።
ንባባት፡ ኤፌ 4፡1-7፥ 1ዮሓ 2፡1-8፥ ግ.ሓ. 8፡5-17፥ ዮሓ፡ 14፡15-31።
ስብከት፡ “ዐረገ ውስተ አርያም፥ ጸዌውከ ጼዋ ወወሃብከ ጸጋከ ለእጓለ እምሕያው፥ እስመ ይክሕዱ ከመ ይህድሩ” መዝ. 88፡18።
የአባ ዳዊት ስብከት ለማዳመጥ RealAudioMP3

 ...»


መዝሙር፡ በሰንበት ዐረገ ሐመረ
ምስማክ፡ ዐረገ እግዚአብሔር በይባቤ፤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን፤ ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ “አምላክ በእልልታ፤ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ፤ ዘምሩ ለአምላክችን ዘምሩ” (መዝ 46፤5-6)
ንባባት፤ ሮሜ 10፤1 እስከ ፍጻሜ፤ 1ኛ ጴጥ 3፤15 እስከ ፍጻሜ፤ የሐዋ ሥራ 1፤1-12፤ ወንጌል፡ ሉቃስ 24፡45 እስከ ፍጻሜየአባ ዳዊት ስብከት ለማዳመጥ RealAudioMP3
 ...»

ፍጻሜዎች 

አስተማሪዎች ተማሪዎች የክልል መስተዳድር አባላት የተለያዩ የማሙያተኞች ማኅበራት የተሳተፉበት በጠቅላላ 200 ሰዎች የሰላም መልእክት ለማድረስ በሚል መርህ ሥር በኢጣሊያ ከፐሩጃ አሲዚ የሚካሄደው የሰላም የእግር ጉዞ የሚያንጸባርቅ የሰላም የእግር ጉዞ በእስራኤልና በእስራኤል በተያይዙት የፍልስጥኤም ክልሎች መካሄዱ ሲገለጥ፣ ይኽ የሰላም የእግር ጉዞ የተለያዩ የሰብአዊ መብትና ክብር ተማጓች ...»


የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት “Cortile dei Gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ በሚል ርእስ ሥር የተመራ የዓለማችን አበይት እና አንገብጋቢ በፍልስፍና በቲዮሎጊያ በሥነ ኅልውና ርእሰ ዙሪያ የሚቀርቡት ጥያቄዎችና መልሶቻቸውንም መሠረት በማድረግ አማኞች እና ኢአማኒያን ሊቃውንትና ምሁራንን RealAudioMP3 የሚያወያይ እምነት እና ምርምር የማይነጣጠሉ የሚደጋገፉ መሆናቸው ለማረጋገጥ ዓልሞ ...»


እ.ኤ.አ. ከመስከረም 12 እስከ መስከረም 15 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢጣሊያ ቶሪኖ ከተማ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው ብሔራው የማኅብራዊ ሳምንት ትኩረት በቤተሰብ ዙሪያ መሆኑ በኢጣሊያ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች የማኅበራዊ ሳምንት አዘጋጅ ኮሚቴ ሊቀ መንበር የካሊያሪ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አሪጎ ሚሊዮና የቶሪኖ RealAudioMP3 ሊቀ ጳጳስ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ቸሳረ ...»


የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ኵላዊት ቤተ ክርስትያን እ.ኤ.አ. ቅዳሜ መስከረም 29 ቀን 2012 ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት በዓል እንዳከበረች የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስ ገብራኤል መልአክ የጋዜጠኞች የመገናኛ ብዙሃን ሠራተኞች በጠቅላላ የመገናኛ ብዙሃን ጠበቃ ቅዱስ በመሆኑ፣ እንደተለመደው በዚህ RealAudioMP3 ዓመታዊ በዓል ምክንያት በራዲዮ ቫቲካን ሕንፃ በሚገኘው ብሥራተ ገብርኤል ጸሎት ቤት፣ ...»


በስዊዘርላንድ ሳን ጋሎ ሲካሄድ የሰነበተው የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ምሉእ ጉባኤ መጠናቀቁ ሲገለጥ፣ የተካሄደው ጉባኤ በዓለማችን ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ፣ ሥነ ምግባራዊ ነክ ጥያቄዎች ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ዝርከ 50ኛው ዓመት የእምነት ዓመት፣ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን RealAudioMP3 ሲኖዶስ በተሰኙት ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ትንተና የተከናወነበት መሆኑ ልኡክ ...»


ማን መሆናችን የዝግቶቹ ሰዓታት ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ የቫቲካን ሬድዮ ክንውን ማገናኛዎች ሌሎች ቋንቋዎች የቫቲካን መታወቂያ ገጽ ሃገረ ቫቲካን የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©. ድረ መስተዳድር / የደራሲያን ስሞች / ሕጋዊ ሁኔታዎች / ማታወቂያ