more languages
መታወቂያ ገጽ
ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ
ዝክረ ነገር
የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት
ዓይነት
የፍቅር ሥራና ትብብር
ቤት ክርስቲያን
ባህልና ኅብረተ ሰብ
የቫቲካን ሰነዶች
ሲኖዶስ
ያንድነት ክንውን
ቤተ ሰብ
ወጣቶች
ሓቅና ሰላም
ፖለቲካ
ሃይማኖትና ውይይት
ሥነ ፍጥረትና ግብረ-ገብነት
ጕባኤ ኣስተምህሮና ጸሎተ መልአክ
ሐዋርያውያን ጕብኝቶች
ኣዳምጡ
በቀጥታ
በመጠየቅ
የዝግቶቹ ሰዓታት
Podcast
ልዩ ስርጭቶች
ከረዲዮ ለረዲዮ
ለመመዝገብ
ሙያዊ አገልግሎት
ቪዲዮ
ድረ-ቲቪ
ቪዲዮአዊ ዜና
ዩቲዩብ
መታወቂያ ገጽ
>
ቤተ ክርስቲያን
> 2012-04-25 14:12:10
ፈረንሳይ
የፈረንሳይ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የአገሪቱ ክርስትያን ምእመናን የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ አንቀጸ ሃይማኖት ትምህርት መሠረት በማድረግ ተፈጥሮን የመንከባከብ ባህል እንዲያጎለብቱ
ጥሪ ማቅረባቸው ሲገለጥ፣ የአገሪት ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በሥነ ምኅዳር ዙሪያ ለሁለት ዓመት የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት የሚመለከተው አንቀጸ ሃይምኖት መሠረት በማድረግ በትሮየስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርክ ስተንገር የተመራ ጥናት በማካሄድ አካባቢና ሥነ ምኅዳር በሚል ርእስ ሥር ባወጣው ሰነድ፣ በዓለማችን ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ፣ ሥነ ምኅዳር የሚመለከተው አንገብጋቢ ጥያቄ ፈጽሞ እንዳይነሳ ወይንም እንዲዘነጋ ማድረጉንም ሰነዱን የጠቀሰው አፒክ የዜና አገልግሎት በማስታወቅ፣ ማኅበረ ክርስትያን በአካባቢው የሚከሰቱት ማኅበራዊ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ቀውሶች እንዲሁም የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ክስተቶች በክርስትያናዊ እምነት አመለካከት ሥር ለማንበብ እንዲችል አቅሙና ክርስትያናዊ አመክንዮ የተከተለ አስተያየት የማቅረብ አቅሙም እንዲያጎለብት በኵላዊት ቤተ ክርስትያን አንቀጸ ሃይማኖት የተደገፈው ስለ ማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት ጠንቅቆ እንዲያውቅ መደገፍ አለበት የሚል ሃሳብ የሰፈረበት መሆኑ ገልጠዋል።
ሥነ ምኅዳር በተመለከተ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በመወጠን ማኅበረ ክርስትያን ሰብአዊ ሥነ ምኅዳር እንዲያስፋፋ ማነቃቃት ሁሉንም የፈጠረው እግዚአብሔር በመጸለይና በማክበር ተፈጥሮን መንከባከብ፣ ፈጣሪን ማክበር ፍጠርት ሁሉ ለመንከባከብ እና ለማክበር የሚያነቃቃና የሚያሳድግ መሆኑ የፈረንሳይ ብፁዓን ጳጳሳታ ሰነድ በማረጋገጥ፣ ክርስትያን ማኅበረሰብ ተቀባይነት ያለው ተፈጥሮና ፍጥረትን የሚያከብር የቤተ ክርስትያን ትምህርት መሠረት ያደረገ የልማት እቅድ ለወጠን በሚካሄደው ጥረት ይተጋ ዘንድ እንዳሳሰቡም አፒክ የዜና አገልግሎት አመለከተ።
Share
Tweet
ማን መሆናችን
የዝግቶቹ ሰዓታት
ለዝግጅት ክፍል ይጻፉ
የቫቲካን ሬድዮ ክንውን
ማገናኛዎች
ሌሎች ቋንቋዎች
የቫቲካን መታወቂያ ገጽ
ሃገረ ቫቲካን
የር.ሊ.ጳ. ሊጡርጊያውያን ሥርዓታት
የዚህ ድረገጽ ይዞታዎች ደራሲ መብት የተጠበቀ ነው ©.
ድረ መስተዳድር
/
የደራሲያን ስሞች
/
ሕጋዊ ሁኔታዎች
/
ማታወቂያ